“ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በአሜሪካ የተፈበረከ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ አግኝተናል” – የኢራን ባለስልጠናት ከኮሮና በሽታ ጀርባ አሜሪካ ዋናዋ ወንጀለኛ ልትሆን እንደምትችል የኢራኑ ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል ኃላፊ መግለፃቸውን RT የተባለው የሩሲያ የዜና ተቋም ዘግቧል፡፡ ኮሮና ቻይናንና ኢራንን ለማጥቃት አሜሪካ የፈበረከችው በሽታ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ብናገኝም ይፋዊ ማስረጃ እጃችን አልገባም ብለዋል የኢራኑ ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል ኃላፊ ሁሴን ሳላሚ፡፡ በመጨረሻ ቫይረሱ የፈበረኩትን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ኢራን በሽተውን ታግላ ትገታዋለች ፤ ለዚህ ቃል እንገባለን ያሉት ሀላፊው ዋሽንግተን ግን ከቫይረሱ ስርጭት ፣ ከዚህ ሁሉ ስቃይና ሞት ጀርባ መኖሯን ሙሉ በሙሉ ካረጋገጥን በሽታውን ወደ አሜሪካ መልሰን እንልከዋለን ሲሉ ዝተዋል፡፡ ምንጭ፦ ETHIO FM 107.8 Posted byHabesha Herald6th Mar 20202nd Apr 2020Posted inUncategorized Share this: Share on X (Opens in new window) X Share on Facebook (Opens in new window) Facebook Like Loading... Related Published by Habesha Herald We get you up to date News from every corner of the world . View more posts