“ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በአሜሪካ የተፈበረከ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ አግኝተናል” – የኢራን ባለስልጠናት ከኮሮና በሽታ ጀርባ አሜሪካ ዋናዋ ወንጀለኛ ልትሆን እንደምትችል የኢራኑ ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል ኃላፊ መግለፃቸውን RT የተባለው የሩሲያ የዜና ተቋም ዘግቧል፡፡ ኮሮና ቻይናንና ኢራንን ለማጥቃት አሜሪካ የፈበረከችው በሽታ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ብናገኝም ይፋዊ ማስረጃ እጃችን አልገባም ብለዋል የኢራኑ ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል ኃላፊ ሁሴን ሳላሚ፡፡ በመጨረሻ ቫይረሱ የፈበረኩትን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ኢራን በሽተውን ታግላ ትገታዋለች ፤ ለዚህ ቃል እንገባለን ያሉት ሀላፊው ዋሽንግተን ግን ከቫይረሱ ስርጭት ፣ ከዚህ ሁሉ ስቃይና ሞት ጀርባ መኖሯን ሙሉ በሙሉ ካረጋገጥን በሽታውን ወደ አሜሪካ መልሰን እንልከዋለን ሲሉ ዝተዋል፡፡ ምንጭ፦ ETHIO FM 107.8

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started