COVID19
ከዋይት ሃውስ ጥቂት ደቂቃዎች ርቀት ላይ ምትገኘው የሚሪላንድ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የመጀመሪያ በቫይረሱ [COVID-19] መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሰዎች በመገኘታቸው የክፍለ ግዛትዋ ሀገረ ገዢ ሌሪ ሆጋን አስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል።
VOA
ኮንትራት ሶስት!
በሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ከባቱ እስከ አርሲ ነጌሌ (የኮንትራት ሶሰት) የግንባታ ሂደት መጓተቱ ተገልጿል።
የመንገዱ ግንባታ ሂደት አሁን ላይ መድረስ ከነበረበት 37 በመቶ አፈፃፀሙ 6 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ መሆኑም ታውቋል።
የፕሮጀክቱ ምክትል አማካሪ የሆኑት ኢንጂነር ካሳሁን ጣሰው የመንገዱ ግንባታ የተጓተተው በግንባታ ግብዓት ፍቃድ ችግር፣ በወሰን ማስከበርና በወረዳ አስተዳደር ትብብር ማነስ መሆኑን ተናግረዋል።
ለግንባታው ግብዓት ለማግኘት ብቻ ከአንድ ዓመት በላይ እንደወሰደም ኢንጂነር ካሳሁን ገልጸዋል። ለመንገዱ ግንባታ የነበረውን አመለካከት ለመቀየር ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት በማድረግ መፍትሄ መምጣቱንም ተናግረዋል።
ኢዜአ
የሶስት ሰው ህይወት ጠፍቷል!
ቦሌ ሞርኒንግ ስታር ሞል በሚገኘው ‘እናት ባንክ’ የሚሰሩ ጥበቃዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የ3 ሰው ህይወት ማለፉን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልፀዋል። ፖሊስ የማጣራት ስራ እየሰራ ይገኛል፤ በአካባቢው አምቡላንስ እየተመላለሰም እንደሆነ የቤተሰባችን አባላት አሳውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia