በመንግስት በኩል እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው 14 የትግራይ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እስካሁን የተለቀቁት 11 ብቻ መሆናቸውን ወፍሪ ሀርነት አስታወቀ።🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ወፍሪ ሓርነት!

ወፍሪ ሓርነት!

በመንግስት በኩል እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው 14 የትግራይ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እስካሁን የተለቀቁት 11 ብቻ መሆናቸውን ወፍሪ ሀርነት አስታወቀ።

ወፍሪ ሀርነት በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ የትግራይ አስረኞችን መብት ለማስከበር የተቋቋመ ኮሚቴ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች፦

• መንግስት የካቲት 16 ቀን 2012 ምሽት ላይ እንዲፈቱ ውሳኔ የተላለፈላቸው 14 ሲሆኑ የተለቀቁት 11 ብቻ ናቸው።

• የተፈቱትም ቢሆን በተንጠባጠበ መልኩ የተለቀቁ ናቸው። ይህ ሂደት ግልፅኝነት የጎደለው እና የታሳሪ ቤተሰቦችን ያሳቀቀ ተግባር ነው።

• መንግስት በወቅቱ ያወጣቸው በነበሩ መረጃዎች 60 ትግራዋይ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ የሚያመላክት የነበረ ቢሆንም እንዲፈቱ ትዕዛዝ የተላለፈላቸው ግን 14 ብቻ ናቸው።

• መንግስት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ካሳለፈላቸው 61 እስረኞች ውስጥም 3 ያልታሰሩ የነበሩ እንዲሁም ሁለቱ ከዚህ በፊት ታስረው ከተፈቱ አንድ ዓመት ያለፋቸው፣ ሰባቱ ደግሞ ጥቅምት ታስረው አሁን የተፈቱ ናቸው።

• ለውጥ ላይ ነን እየተባለ አሁንም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትግራይ የፖለቲካ እስረኞች በፌደራል፣ በክልሎች እና በሌሎች ድብቅ እስር ቤቶች ላለፉት ሁለት ዓመታት ታስረዋል፤ መንግስት እነዚህን እስረኞች ሊፈታ ይገባል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started