በሞረትና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሄደ ቡድን ላይ ጥቃት ደረሰ!🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በሞረትና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሄደ ቡድን ላይ ጥቃት ደረሰ!

በአማራ ክልል ሞረትና ጅሩ ወረዳ፣ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጡ የመጡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሐይማኖት ስብከት ለምን ያካሂዳሉ በሚል ጥቃት እንደደረሰባቸው የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ተናገሩ።

ወደ ከተማዋ ያቀናው የሕክምና ቡድን 18 የውጪ አገር ዜጎች የተካተቱበት ከ200 በላይ አባላት ያሉት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ወጋየሁ ቦጋለ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ይልማ ሙሉጌታ በበኩላቸው በእነዋሪ ከተማ ለ20 ዓመት የነበረ ቤተ እምነት ላይ ጥቃትና ዘረፋ መፈፀሙን አረጋግጠዋል።

መጋቢ ይልማ አክለውም ጥቃቱ የተፈፀመው በሐይማኖት አክራሪዎች ነው ያሉ ሲሆን ንብረቶች መዘረፋቸውን፣ ሦስት ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል እንደሚገኙ እና ቃጠሎ መፈፀሙን ተናግረዋል።

More https://telegra.ph/BBC-03-11-2

ምንጭ፦ BBC

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started