

የ20/80 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለዕድለኞች ሊተላለፉ ነው!
የተገነቡት “በኦሮሚያ ክልል ላይ ነው” በሚል ውዝግብ ተቀስቅሶባቸው ከነበሩ የአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ ሰላሳ ሁለት ሺህው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ሊተላለፉ እንደሆነ ሪፖርተር ዘግቧል።
እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ የኮንዲሚኒየም ቤቶቹን ውዝግብ እንዲያጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ተውጣጥቶ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ ዕጣ ከወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 9,000 ያህሉ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መገንባታቸውን አረጋግጧል።
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ!
በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ሰሞኑን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተያዘው ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡
ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ተነጋግሮና መፍትሔ አስቀምጦ ስምምነት ላይ ሳይደረስ፣ ቤቶቹን ለዕድለኞቹ ለማስተላለፍ ውል መፈጸም በቀጣዩ ሒደት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡
More https://telegra.ph/Reporter-03-11
ሪፖርተርጋዜጣ
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ