Corona updates

  • በአሁኑ ሰአት ከቻይና በተጨማሪ እንደ ጣሊያን፣ ኢራን፣ ደቡብ ኮሪያ እና የመሳሰሰሉ ሀገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ ተጨማሪ ክትትሎች እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።
  • ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሀገራት የሚመጡ መንገደኞችን ቅፅ በማስሞላት እና አድራሻቸውን በመያዝ በስልክ ተጨማሪ ክትትሎች እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።
  • እስካሁን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 1 ሺህ 20 መንገደኞች ተጨማሪ ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን፥ 1 ሺህ 93 መንገደኞች ደግሞ በስልክ ከትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
  • ጤና ሚኒስቴር ቫይረሱ ቢከሰትም በፈጥነት መቆጣጠር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን፥ የሆስፒታል ዝግጅት፣ የግብአት እና የባለሙያዎች ዝግጅትም በስፋት እየተሰራበት ነው።
  • የኮሮና ቫይረስ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን የሚያሳይ እና የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ቫይረስ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ላይ መዘናጋት አንደሌለበት ማሰስቢያ ተሰጥቷል።
  • ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ መረጃዎች ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ መረጃዎች ትክክለኛ መሆናቸውን በማረጋገጥም የበኩሉን ደርሻ እንዲወጣ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
  • መላው ህብረተሰብ ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ቀድሞ ለመከላከል የግል ንፅህናን መጠበቅ እና ንክኪዎችን መቀነስ ላይ ትኩረት ማደረግ አለበት ተብሏል።
  • ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ጋር በተያያዘ የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ሲመለከት ሆነ መረጃዎችን እና እርዳታዎችን ለማግኘት ወደ 8335 መደወል እንዳለበት መልዕክት ተላልፏል።

DrLiaTadesse #ኤፍቢሲ #ጤናሚኒስቴር

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started