“ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ ነው!” – ዛሬ ሹመቱን ከተቃወሙ የምክር ቤት አባላት🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

“ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ ነው!” – ዛሬ ሹመቱን ከተቃወሙ የምክር ቤት አባላት

የዛሬው የአራቱን ሚኒስትሮች ሹመት 21 የሕወሓት አባላት ተቃውመውት ነበር፡፡ ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ እንደሆነ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሕወሓት ያፈራውን ሀብት ለመቀራመት የሚደረግ ሹመት ነው የሚሉ ተቃውሞዎችም ተሰምቷል፡፡

ሌሎቹ የምክር ቤት አባላት ደግሞ በተሿሚዎቹና በሹመቱ ላይ የቀረበውን ትችት ያስተባበሉ ሲሆን ፣ ‹‹ሚኒስትሮቹ የሚሾሙት ላለፉት ዓመታት የተዘረፈ ሀብትን ለማስመለስ ነው፤›› ሲሉ ወ/ሮ ብርቱካን ታደሰ የተባሉ የምክር ቤቱ አባል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዳባ ደግሞ ዶ/ር ሊያ ከትግራይ ብሔር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ከዚህ ቀደም ሚኒስትሮችን ለመሾም የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ቡራኬ ያስፈልግ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ሹመት መስጠት በመጀመራቸው ምክንያት የቀረበ ተቃውሞ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started