
“በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው” – የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
የFDRE ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እና የሰራዊቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎችም ተሳትፈዋል።
በጉብኝታቸውም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እየተገነባ ያለውን የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት