
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 547 የምርጫ ክልሎች ይፋ አድርጓል!
ትግራይ 38፣ አፋር 8፣ አማራ 138፣ ኦሮሚያ 178፣ ሶማሌ 23፣ ቤኒሻንጉል 9፣ ደቡብ 123፣ ጋምቤላ 3፣ ሀረሪ 2፣ ድሬዳዋ 2 እንዲሁም አዲስ አበባ 23 ለፌደራል ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ይኖራቸዋል።
አሁን ያሉት የምርጫ ክልሎች በ1976 ዓ.ም በደርግ ዘመን የተካሄደውን የህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት በማድረግ በ1985 ዓ.ም መካለላቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል።