ለ እረጅም ጊዜ እጣ ወጦላቸው ያልተላለፉ የ 20/80*የ ኮንዶሚኔም ቤቶች ለ እድለኞች እንዲተላለፉ እና ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደረገላቸው

በ13ኛው ዙር የ20/80 የኮንዶሚኒየም ዕጣ የደረሳቸው ዕድለኞች ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደረገላቸው
.
ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለ13ኛ ጊዜ ዕጣ የወጣባቸውና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የደረሳቸው ዕድለኞች፣ በየወረዳቸው ቀርበው ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደረገላቸው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማትና አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ባስተላለፈው መመርያ መሠረት፣ ክፍላተ ከተሞቹ ከዕድለኞቹ ጋር ውል እንዲዋዋሉ ለወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች መመርያውን አስተላልፈዋል፡፡
ከክፍላተ ከተሞቹ መመርያ የተላለፈላቸው የወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች፣ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ውል ለመዋዋል ወደ ጽሕፈት ቤቶቹ ሲሄዱ ማሟላት የሚገባቸውን መሥፈርቶች በዝርዝር አሳውቀዋል፡፡
በመሆኑም ዕጣው የደረሳቸው ዕድለኞች የታደሰ መታወቂያ፣ ያገባ(ች) ከሆኑ የጋብቻ ሰርተፊኬት፣ ባልና ሚስት ከሚኖሩበት ወረዳ በስማቸው የግልም ሆነ የመንግሥት ቤት እንዳላቸው ወይም እንደሌላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡
ያላገባ(ች) ከሆነ በስድስት ወራት ውስጥ የታደሰ ሰርተፊኬት፣ የባንክ ደብተር፣ የተመዘገበው ዕድለኛ ከሌለ(ች) ሕጋዊ ውክልና ያለው(ላት) መሆን እንዳለበትም ተገልጿል፡፡ ከላይ የተጠቀሱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ዕድለኞች፣ ከክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ቅጽ 09 በመያዝና ዝርዝር ማስረጃዎቹን ፎቶ ኮፒ ይዘው በየወረዳቸው በመቅረብ፣ መዋዋል የሚችሉ መሆኑን ወረዳዎች አስታውቀዋል፡፡
የ13ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣው የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. መሆኑ ይታወሳል፡፡ ዕጣው በወጣ ማግሥት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በተለይ በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተገነቡበት ኮዬ ፈጬ አካባቢ በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት፣ የዕጣው ዕድለኞች ሳይዋዋሉ እስካሁን ቆይተዋል፡፡
መንግሥትም ጉዳዩ ከወሰን ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ለማጣራት፣ ከከተማ አስተዳደሩና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ ኮሚቴ በማዋቀር አስጠንቷል፡፡ በውጤቱም ዘጠኝ ሺሕ ቤቶች የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መሆኑን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡
ምንም እንኳን የኮሚቴው ጥናት ውጤት ለሕዝብ ይፋ ባይደረግም፣ ከዓመት ቆይታ በኋላ ዕጣ የደረሳቸው ዕድለኞች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ተዋውለው፣ ቀጣይ የማስተዳደር ሒደት በክልሉ ሥር ሊሆን እንደሚችል መገለጹን በረቡዕ ዕትም መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ውል ማዋዋል በየወረዳው መጀመሩም ተጠቁሟል፡፡
15 March 2020
ታምሩ ጽጌ
ሪፖርተር

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started