
በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ወደ ማቆያ ቦታ በመውሰድ ላይ ሳለ አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠው ግለሰብ በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፌዴራል እና ከለጋምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እንዲሁም የፀጥታ መቃቅሩ የጋር ትብብር ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡
ግለሰቡ በለጋምቦ ወረዳ 07 ቀበሌ ሰላም በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት ከሀገር ውጭ የወጣና አሁን የተመለሰ ነው፡፡
የለጋምቦ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት አበባው እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ ከውጭ ሀገር ተመልሶ አዲስ አበባ ሲደርስ የበሽታው ምልክቶች ታይተውበት ወደ ምርምራ በመወሰድ ላይ እያለ አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪው ግለሰብ በትናንትናው እለት ደሴ ከተማ ያደረ ሲሆን ዛሬ ጧት በሳይንት አጅባር አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተሳፍሮ ገነቴ ከተማ ለመድረስ ከአራት ኪሎ ሜትር ያልበለጠ ጎዞ ሲቀረው ወለቃ ወንዝ ላይ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ ጌትነት አስረድተዋል፡፡
ምንጭ፦ Legambo communication