COVID19
የኢፌዲሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በተመለከተ መንግስት በሰጠው ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ሰራዊቱን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ስጥተዋል።
ጄኔራል አደም መሃመድ እንደገለፁት የመከላከያ ሰራዊት በሃገር ውስጥም ይሁን በሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት ራሱን መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ሰራዊቱ ሃገርና ህዝብን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች የመከላከል ተልዕኮውን መወጣት የሚችለውም ጤንነቱ የተጠበቀ ሲሆን ብቻ እንደሆነ ያብራሩት ጄኔራል አደም የቫይረሱን [COVID-19] ስርጭት ለመግታት በየደረጃው ግብረ ሃይል መቋቋሙን ገልፀዋል።
ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት