ሃሌሉያ ጠቅላላ ሆስፒታል ዛሬ ረፋድ በሰጠው መግለጫ ነፃ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። በመሆኑም የቫይረሱ ስጋት ያለባችሁ ወይም መመርመር የምትፈልጉ ሰዎች በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ እየመጣችሁ በነጻ መመርመር ይችላሉ ብሏል።
ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎችን በነጻ በመመርመር ላይ ሲሆን እስካሁን ስድስት ሰዎች የበሽታው ምልክት በማሳየታቸው መንግስት ተጠርጣሪዎቹን ወደለይቶ ማቆያ ክፍል አስገብቶ እንዲያክም አሳልፎ መስጠቱን ገልጿል።
ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዳደርግ ከፈቀደልኝ የህክምና መሳሪያዎችን ከውጭ አገራት አስገቼ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
ሆስፒታሉ ዛሬ ረፋድ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩን እና ለዚህ ስራው 300 ሺህ ብር መመደቡን እንዳስታወቀ መዘገባችን ይታወሳል።
በመሆኑም የቫይረሱ ስጋት ያለባቹህ ወይም መመርመር የምትፈልጉ ሰዎች በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ እየመጣችሁ በነጻ መመርመር ይችላሉ ብሏል።
Source – Mereja.com