sport የተቀነጫጨበ ዜና🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ማክሰኞ ጠዋት በትልልቆቹ የአውሮፓ ጋዜጦች ላይ የወጡ የተጠናቀቁ፣ የተቃረቡ የዝውውርና ሌሎችም አጫጭር ወሬዎች! ዜናዎቻችን ሁሌም በቅድሚያ እንዲደርሷቹ ላይክ፣ ኮመንትና ሼር ማድረጉን አይርሱ!
───────────────
─────────────
▷ ባየር ሊቭርኩሰን እና ቼልሲዎች በካይ ሃቭሬዝ የ€100m ዝውውር ሂሳብ ላይ ከስምምነት ደረሱ። ቼልሲዎች €80m ሂሳቡን በቀጥታ የሚከፍሉ ሲሆን ተጨማሪ + €20m ሂሳብ ደግሞ እንደ ስኬቱ እየታየ የሚከፈል ይሆናል። በስታምፎርድ ብሪጅ የአምስት አመታት ውል ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል። (Fabrizio Romano)
───────────────
─────────────
▷ እንዲሁም ቼልሲዎች የሻምፒየንስ ሊጉ የፍፃሜ ተፋላሚውን ቲያጎ ሲልቫን ለማስፈረም ተስማምተዋል። ብራዚላዊው ከዘጠኝ አመታት የፓሪስ ቆይታ በኃላ ወደ ስታምፎርድ ብሪጁ ክለብ በነፃ ዝውውር ላማምራት ተስማምቷል።
(David Ornstein)
───────────────
─────────────
▷ ቼልሲዎች ጀርመናዊውን የ21 አመት አማካይ ካይ ሃቭሬዝ እና የ35 አመቱን ብራዚላዊ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫን ለማስፈረም ከተስማሙ በኃላ ከዚህ በፊት በክለቡ ካደረጉት ዝውውር በላይ ትልቅ የዝውውር ገንዘብ ያወጡበት ክረምት ይሆናል። (The Times)
───────────────
─────────────
▷ ኪንግስሌይ ኮማን የመጀመሪያ እቅዳቸውን ጃደን ሳንቾን የማያዛውሩ ከሆነ ሁለተኛ የዝውውር እቅዳቸው አድርገው ወደ ኦልትራፎርድ ሊያመጡት ማንቸስተር ዩናይትዶች አቅደዋል። (men)
───────────────
─────────────
▷ የጃደን ሳንቾ ማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውር አሁን ሊሆን ይችላል፣ አሁን ካልሆነ ግን ፈፅሞ ሚሆን አይመስልም። (Dharmesh Sheth, Sky)
───────────────
─────────────
▷ ዶኒ ቫን ደ ቤክ በዚህ ክረምት አያክስን መልቀቁ አይቀርም። ከፕሪሚየር ሊጉ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ለማድመጥ ዝግጁ ነው። እስካሁን ከእንግሊዝ ክለቦች የቀረበለት ምንም ጥያቄ የለውም ሆኖም ማንቸስተር ዩናይትዶች ፍላጎት እንዳላቸው ተገልፆአል። (sky sports)
───────────────
─────────────
▷ ማንቸስተር ዩናይትዶች የአንሱ ፋቲህን ውል ማፍረሻ ሂሳብ £153m ለመክፈል ተዘጋጅተዋል። ዩናይትዶች የጀደን ሳንቾ ዝውውር ላይ ከቦሩሲያ ዶርትመንዶች ጋር ስምምነት ማድረስ ስላቃታቸው ፊታቸውን ወደ ባርሴሎናው ታዳጊ ኮከብ ላይ አዙረዋል። (Mundo Deportivo)
───────────────
─────────────
▷ ገብርኤል ማጋልሄስ የህክምና ምርመራውን በአርሰናል በማድረግ ላይ ይገኛል። ትላንት ለንደን የገባ ሲሆን ለዝውውሩ አርሰናሎች €26m በቀጥታ እና + €4m እንደስኬቱ የሚከፈል ሂሳብ ለሊሎች ይከፍላሉ። ህክምናውን ካለፈ በኃላ ለሁለት ሳምንታት ኳራንታይን እንደሚገባ ይጠበቃል።
(David Ornstein)
───────────────
─────────────
▷ ገብርኤል ማጋልሄሽ በአምስት አመት ኮንትራቱ ላይ ዛሬ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
(le10sport)
───────────────
─────────────
▷ አርሰናሎች ጆናታን ዲንዜይን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል። ተጭዋቹ የቀድሞ የቶተንሃም አካዳሚ ተጭዋች ነበር። (Dinzeyi Jonathan)
───────────────
─────────────
▷ PSGዎች የአርሰናሉን ፈረንሳዊ አማካይ ማቲዎ ጉንዲዚን ስለሚያስፈርሙበት ሁኔታ እያጤኑ ነው። (lequipe)
───────────────
─────────────
▷ ሚካኤል አርቴታ የአርሰናሉን የቀድሞ ኮከብ ዴኒስ ቤርካምፕ የፍሬድሪ ሉምበርግ ምትክ በማድረግ የክለቡን አሰልጣኞች ቡድን ስታፍ እንዲቀላቀልለት ይፈልጋል። (Mark Irwin)
───────────────
─────────────
▷ ፊሊፕ ኩቲንዎ የባርሴሎና ህይወቱን በሮናልድ ኩይማን ዘመን እንደ አዲስ ሀ ብሎ መጀመር ይፈልጋል። ለቦታው በመፋለም ወደ ቌሚ አሰላለፍ ለመመለስና የቡድኑ ቁልፍ ተጭዋች ለመሆን ጥረት ያደርጋል። (Roger Torello)
───────────────
─────────────
▷ ዎልቭሶች የአርሰናሉን ኤንስሌይ ሚትላንድ ኔይልስን ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ድርድር በማድረግ ላይ ናቸው። የአራት አመት ውል ያስፈርሙታል። (Sky Sports)
───────────────
─────────────
▷ አስቶንቪላዎች የአትሌቲኮ ማድሪዱን እንግሊዛዊ ተመላላሽ ተከላካይ ኬራን ትሪፒየርን በዚህ ክረምት የዝውውር መስኮት ላይ ለማምጣት ይፈልጋሉ።
(Daily Mail)
───────────────
─────────────
▷ ማንቸስተር ሲቲዎች ጆን ስቶንስን ቼልሲዎች በ£20m ሂሳብ ብቻ እንዲያስፈርሙት አቅርበውላቸዋል። ሆኖም ለዝውውሩ ትልቅ እንቅፋት ይሆናል ተብሎ ሚጠበቀው ተከላካዩ በኢትሃድ የሚከፈለው ሳምንታዊ ደሞዝ ከፍተኛ መሆኑ ነው። (caught offside)
───────────────
─────────────
▷ ካሊዱ ኩሊባሊ የማንቸስተር ሲቲ ዝውውሩን ለመጨረስ ሲመጣ ‘የሚለብሰው ሱፍ’ ተዘጋጅቶ ተቀምጧል። (La Gazzetta dello Sport)
───────────────
─────────────
▷ | አውሬሎ ዲ ላውረንቲንስ ስለ ኩሊባሊ ዝውውር: “ትልቅ የዝውውር ሂሳብ ካልቀረበ በቀር አይለቅም” (Radio Punto Nuevo)
───────────────
─────────────
▷ ኪውማን ለሱዋሬዝ ትላንት ደውለውለት ነበር፣ እንደማይፈልጉት በግልፅ ነግረውታል። የሱ ክለቡን መልቀቅ ለላውታሮ ማርቲኔዝ መምጣት ወሳኝ ነው። ባርሳዎች በቀጣይ ከኡራጓዊው ተጭዋች ጠበቆች ጋር ይገናኛሉ። ኮንትራቱንም በይፋ ያቌርጡታል።
(Roger Torello)
───────────────
─────────────
▷ ምናልባት ባርሴሎናዎች የላውታሮ ዝውውር ማያጠናቅቁ ከሆነ እንደ እቅድ ለ የተያዘው ሜምፒስ ዴፓይ ነው። ኔልሰን ሴሚዶ እና ጆርዲ አልባ በበኩላቸው በክለቡ ይቆያሉ ተብሏል።
(ffpolo)
───────────────
─────────────
▷ የቀድሞው የኢንተር ሚላን ባለቤት ማሲሞ ሞራቲ እንዳሉት ከሆነ የቀድሞ ክለባቸው የባርሴሎናውን የ33 አመት አርጀንቲናዊ አጥቂ ሊዮኔል ሜሲን ለማስፈረም እየጣሩ ነው። (AS – in Spanish)
───────────────
─────────────
▷ ኤቨርተኖች ለ29 አመቱ ብራዚላዊ አማካይ አለን ዝውውር ለናፖሊ የ £31.5m ሂሳብ ለመክፈል ከስምምነት ላይ ደረሱ። (Daily Express)
───────────────
─────────────
▷ ማንቸስተር ዩናይትዶች ፖርቹጋላዊውን የ24 አመት ግብ ጠባቂ ጆኤል ፔሬራን ለሃድስፊልድ ቶውን በውሰት ውል ለመስጠት ተዘጋጅተዋል። (The Sun)
───────────────
─────────────
▷ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር Uefa በቀጣይ የአውሮፓ ጥሎ ማለፍ ውድድሮቹን በአንድ ቦታ በአንድ ጨዋታ ፎርማት ለማድረግ እያጤኑት ነው። ከሜዳ እና ውጪ ፎርማት የተለየ ቅርፅ ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል። (Tele Football)
───────────────
─────────────
▷ DEAL DONE: ኒውካስሎች ጄፍ ሄንደሪክን በነፃ ዝውውር አስፈረሙ። የአራት አመት ኮንትራት ተፈራርሟል። (NUFC)
───────────────
─────────────
▷ DEAL DONE: ሌስተር ሲቲዎች የናምፓልይስ ሜንዲን ኮንትራት እስከ 2022 ድረስ አራዘሙ። (LCFC)
───────────────
─────────────
▷ CLOSE DEALS: ጆርዳን ሁጊል ከዌስትሃም ወደ ኖርዊች በ£5m ሂሳብ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ተቃርቧል። (Sky Sports)
───────────────
─────────────
▷ DEAL DONE: ጀምስ ማዲሰን በሌስተር ሲቲ የሚያቆየውን የአራት አመት ውል ተፈራርሟል። (LCFC)
───────────────
─────────────
▷ DEALS DONE: አርሰናሎች ፓብሎ ማሪን እና ሴድሪች ሶአሬስን በቋሚ ውል አስፈረሙ። የውሉ ዝርዝር አልተገለፀም። (Arsenal)
─────────

Published by Habesha Herald

We get you up to date News from every corner of the world .

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started