ዘመድኩን በቀለ ታፈኑ ስለተባሉት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ቀጣዩን መልክት አስተላልፏል 💚💛❤

ዜና ሊቃነ ጳጳሳት !!
~★★~
• ይሄ እኔ ያለኝ መረጃ ነው። መፍትሄው እውነት መነጋገር ነው። አርነት የሚያወጣው እውነት መናገር ነው። ነጭ ነጯን መናገር እንጂ ዙሪያ ጥምጥም አያስፈልግም ባይ ነኝ።

ETHIOPIA | ~ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል።

•••
ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ፥
“ … የሶማሌ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሶማሌ ክልል ተፈጥሮ የነበረውን የአሸባሪዎች ጥቃት ተከትሎ ወደ ሃገረ ስብከቱ ለመመለስ ባለመፍቀዳቸውና በመፍራታቸው ምክንያት ወደ ሶማሌ ሃገረ ስብከት የሚሄድ ሊቀጳጳስ በጠፋ ጊዜ የካናዳ ሀገረ ስብከታቸውን ትተው በፈቃደኝነት እሳት ውስጥ የገቡትና ኋላም የሐረሩ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሰላማም በህክምና ምክንያት ምሥራቅ ሀረርጌን ማስተዳደር ባልቻሉ ጊዜ ፥ ሱማሌንም ሀረርጌንም ደርበው፣ በየመቃብር ቤቱ ተኝተው እያደሩ።ገጠር ድረስ በመጓዝ በህይወት ዘመናቸው ጳጳስ አይተው የማያውቁ ምእመናንና ካህናትን በመጎብኘት፣ ከመንግሥት ባለሥልጣናትም ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው የቤተ ክርስቲያንን መደፈር በጽኑ ተቃውመው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀና እንድትል ያደረጉ አባት ናቸው ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ።
•••
ብፁዕነታቸው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ነው በድንገት በገጠማቸው ህመም ምክንያት በሀገረ እስራኤል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከትናንት ወዲያ በመጠኑ ተሽሏቸው ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት። ከብፁዕነታቸው ጋር ተደዋውለን እንደተነጋገርነውም አሁን ላይ በመጠኑም ቢሆን ተሽሎኛል፣ ደግሞም የሚመጣውን መከራም ከህዝቤ ጋር ብቀበል ይሻለኛል ዘመዴ ነበር ያሉኝ። ብፁዕነታቸው አሁን አዲስ አበባ ናቸው።
•••
ብጹዕ አቡነ ሩፋኤል ፦
“ … በብዙ ክርክርና ውዝግብ የተሾሙ አባታችንም ጓደኛችን ናቸው። በቀደመው የህወሓት ዘመን በጋምቤላ ለሚኖሩ የህወሓት ባለሃብቶች ጥቅም ሲባል የጋምቤላ ክልል መንግሥት ለሲኖዶሱ ደብዳቤ ጽፎ በግድ ሲመተ ጵጵስናውን እንዲቀበሉ የተደተጉም አባት ናቸው። በጋምቤላም፣ በደቡብ ሱዳንና አሁን ደግሞ በምዕራብ ኢትዮጵያ አሶሳን ደርበው እንዲይዙም የተደረጉ አባት ናቸው።
•••
አባ ተክሌ ይፈጥናሉ። ይሄ ፍጥነታቸው ከአረጋዊያኑ ሊቃነጳጳሳት ጭምር ተግሳጽና ሃዘንም ይደርሳቸው ነበር። ሲበዛም የዋሕም ናቸው። እሳቸውን ተጠግተው ጥቅም ማጋበስ የሚፈልጉም የትዬለሌ ናቸው። በተለይ ምድረ ተሃድሶ እንደ ዝንብ ነው የሚወራቸው። ጎንደር ተወልደው አዲስ አበባ ሰባራ ባቡር አድገው ኋላም መቱ ኢሊባቦር ያደጉት ብፁዕነታቸው ለውጡን ተከትሎ ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ኦሮሞ ነው በሚል እሳቤ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ በመጻፍ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጭምር ዐማራ የተደረግኩት በስህተት ነው ኦሮሞ የሚል የዘር መታወቂያ እንዲሰጠኝ ስል በትህትና አመለክታለሁ በማለት ለኦሮሞ ያላቸውን ፍቅር በአደባባይ የገለፁም ምስኪን አባት ናቸው።
•••
ታዲያ አሁን እኚሁ ሊቀጳጳስ ባመኑት የኦሮሞ መንግሥትና፣ በፈቃደኝነት በደብዳቤ ጽፈው ኦሮሞነትን የተቀበሉት የኦሮሞ መንግሥት ህዝብ አደጋ ላይ ጥሏቸው ተገኝተዋል። ቄሮና የኦሮሚያ ፖሊስ ነን የሚሉ አካላት ( አንዳንዶች ሽፍቶች ናቸው ይላሉ) ሊቀጳጳሱን በጋራ አደጋ አድርሰውባቸው አሁን ሊቀጳጳሱ ሆስፒታል ተኝተዋል ተብሏል።
•••
ነገሩ እንዲህ ነው። አቡነ ሩፋኤል ከአዲስ አበባ ተነሥተው ከሹፌራቸው ጋር ወደ አሶሳ ሀገረ ስብከታቸው ጉዞ ይጀምራሉ። [ ይሄን ጉዞ የአሶሳ ምእመናን ቢቃወሙትም፣ ወደ ሀገረ ስብከታችን ድርሽ እንዳይሉብን ብለው በአካልም፣ በስልክም፣ በደብዳቤም እንዳሳሰቧቸው ተነግሯል] ሆኖም ሊቀጳጳሱ ጉዞ ወደ አሶሳ ቀጥለዋል። በጉዞአቸውም ላይ እግረ መንገዳቸውን 900ሺ ብርም በሻንጣ ይዘዋል። ጉዞው ቀጠለ፥ ቀጠለና ምእራብ ወለጋ አባ ሴና በተባለ ቦታ ላይ እንደደረሱ፣ የተደራጁ ቄሮዎች እና ፖሊሶች[ ሽፍቶችም የሚሉ አሉ] ሊቀጳጳሱን አሳፍራ ወደ ደምቢዶሎ በመገስገስ ላይ ያለችዋን መኪና ያስቆማሉ። “ ውረድ? አልውረድም። ማነህ? ምንድነህ መባባል ተጀመረ። ጭቅጭቅ ይፈጠራል። ቄሮና ሽፍታው መኪናዋን መፈተሽ ይጀምራሉ። ብር በሻንጣ ያገኛሉ። ጥያቄና መልስ ተጀመረ። የት ነው? ይሄን ያህል ብር ይዘህ የምትሄደው? አይመለከታችሁም። በመሃል ጭቅጭቁ እየከረረ መጣ። ይሄን ጊዜ የአቡኑ ሹፌር የማይገባ እርምጃ ወሰደ። ክላሽ ከመኪናው አውጥቶ ወደ ላይ ተኮሰ። ይሄን ጊዜ ድብልቅልቁ ወጣ። ነገር ተበላሸ።
•••
ታጣቂዎቹ በያዙት ዱላ ሊቀጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልን እግራቸው ላይ ደጋግመው ቀጠቀጧቸው። ሊቀጳጳሱ ወደቁ። ተኩሱን የሰማ ህዝብ ተሰበሰበ። መከላከያም ደረሰ። ጳጳሱን ወደ ህክምና ሹፌሩንም ያልተፈቀደ ህገወጥ የጦር መሣሪያ በመያዝ በሚል ወደ ካምፕ ወሰዱት። አሁን ሊቀጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል እዚያው ምዕራብ ወለጋ በአንድ የግል ህክምና ተቋም በመታከም ላይ ይገኛሉ።
•••
ሾፌሩ መሣሪያው የእኔ አይደለም በማለቱ ለጊዜው ተለቋል። የሊቀጳጳሱ መኪና ተጎድታለች። ሊቀጳጳሱ በደረሰባቸው የዱላ ድብደባ ምክንያት በህክምና ላይ ናቸው። መከላከያ ደርሶ የተዘረፈውን 900 ብር ለማስመለስ ጥረት ቢያደርግም ብሩን የያዘው አካል የብሩን ምንጭ ሳናውቅ፣ ብሩ ለምን ጉዳይ በዚህ መልኩ እንደሚሄድ ሳንረዳ አንለቅም ብሏል። እኔ ያለኝ መረጃ ይሄው ነው። የሌላውን አላውቅም። አከተመ።
•••
ጠረጋው ግን ከላይ ነው የሚጀምረው የተባለውን አውቃለሁ። ከላይ ከቤተ ክህነቱ። ከላይ ነው የሚጀምረው። እንደ መጽሐፉ ቃል በትህትና የማይኖሩ ሁሉ እገሌ ወእገሌ ሳይሉ ይጠረጋሉ። ይጋለጣሉ። ምንም መሸፋፈን አያስፈልግም። ሙዳየ ምጽዋቱን የዘረገፉ፣ ታቦቱን ያቀለሉ፣ የሸጡ፣ ቤተ ክርስቲያንን ያራቆቱ፣ ያስለቀሱ፣ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች በሙሉ ይጠረጋሉ። ጅራፉ ከቤተ መቅደሱ ነው የሚጀምረው። እስቲ አሁን እናየለን። በተዘረፈ የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ በሠራኸው ቤት ተንደላቀህ ትኖር እንደሁ እናያለን። በባንካችን ያጠራቀምነው የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ያድነን እንደሁ እናያለን። ለጳጳስ መስቀል እንጂ ክላሽ ምን ያደርግለታል?
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መጋቢት 9/2012 ዓም።
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Breaking News #ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በኦሮሚያ ክልል ጊምቢ አካባቢ ለጊዜው ባልታወቁ ምናልባትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ታፍነው እንደተሰዱ ታወቀ።💚💛❤

ሰበር ዜና
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በኦሮሚያ ክልል ጊምቢ አካባቢ ለጊዜው ባልታወቁ ምናልባትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ታፍነው እንደተሰዱ ታወቀ።
የጋምቤላና የምዕራብ ወለጋ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ማንነታቸው ለጊዜው ባልታወቁ ኃይሎች መታፈናቸው ታወቀ።
በጵጰስና ደረጃ በታጣቂ ኃይሎች አፈና ሲካሄድ በታሪክ የመጀመሪያው ነው።
በዚሁ አካባቢ 17 የሚሆኑ የአማራ ተማሪዎች ከታፈኑ ከ106 ቀናት በላይ መሆኑ ይታወቃል። መንግስትም ነገሮችን አድበስብሶ ለማለፍ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ብዙዎች ትችታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ጃዋር መሀመድ ስለ #CORONA ተከታውን መልክት አስተላልፏል💚💛❤

የኮሮና ቫይረስ አለምን እያመሳት ነው። በቫይርሱ የሚያዙ እና የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ነው። በሀገራችን እስካሁን የታወቁ ኬዞች 6 ናቸው። ቫይርሱን ለመግታት እስካሁን በምንግስት እና ህዝብ እየተደረገ ያለው ርብርብ ጥሩ ነው፡: ሁለት ነገሮች ላይ መንግስት እና ህዝብ ውሳኔ መስጠት የሚያስፈልግ ይመስለኛል።
1) በሀገራችን ህዝቡ በገራ በዛ ብሎ ፈጣሪውን እንደሚያመልክ ይታወቃል። ይህ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭነትን ይጨምራል። ስለዚህ የሀይማኖት አባቶች ስለ ጁምዓ እና የሰንበት ጸሎቶች ወስነው ምዕመናኑን ማሳወቅ አለባቸው።
2) ሳምንታዊ ገበያዎች ህዝባችን ከገጠር በሺዎች ተምሞ የሚገበያይበት ነው። ይህ ደግሞ ቫይረሱ በቀላሉ እንዲስፋፋ እና ወደገጠር እንዲገባ እድል ይሰጠዋል። ስለዝህ መንግስት በገበያ ጉዳይ ላይ አፋጣኝ ወሳኔ አሳልፎ ለህዝቡ ማሳወቅ አለበት።

#የኢፌዲሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በተመለከተ መንግስት በሰጠው ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ሰራዊቱን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ስጥተዋል።💚💛❤

COVID19

የኢፌዲሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በተመለከተ መንግስት በሰጠው ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ሰራዊቱን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ስጥተዋል።

ጄኔራል አደም መሃመድ እንደገለፁት የመከላከያ ሰራዊት በሃገር ውስጥም ይሁን በሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት ራሱን መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ሰራዊቱ ሃገርና ህዝብን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች የመከላከል ተልዕኮውን መወጣት የሚችለውም ጤንነቱ የተጠበቀ ሲሆን ብቻ እንደሆነ ያብራሩት ጄኔራል አደም የቫይረሱን [COVID-19] ስርጭት ለመግታት በየደረጃው ግብረ ሃይል መቋቋሙን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

የ ታጋች እህት በ ፌደራል ፖሊስ ተይዛ ወደ አዲስ አበባ መወሰዷ መረጃ እየወጡ ነው ። 💚💛❤

በ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተደረገው እገታ ከ 3 ወር በላይ አልፎታል መንግስት ያለው ነገር የለም ። ይበልጥ በመንግስት አጋላት የ ታጋች ቤተሰቦችን የማዋከብ ነገር ይታያል ተብሏል ። ዝርዝር መረጃ ሲደርሰን እናቀርባለን

#በጣሊያን ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ታውቋል ለ ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን💚💛❤

ህይወታቸውን በ ኮሮና ቫይረስ ያጡት ኢትዮጵያዊ ሰዉዪ እኒህ ነበሩ ። ነፍስ ይማር

#በጣሊያን ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ታወቀ”የመጣውን (ሀዘን) ለመቻል ጥረት አደርጋለሁ። …በቻላችሁት ሁሉ ጥንቃቄ አድርጉ”💚💛❤

በጣሊያን ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ታወቀ
“የመጣውን (ሀዘን) ለመቻል ጥረት አደርጋለሁ። …በቻላችሁት ሁሉ ጥንቃቄ አድርጉ”

[የሟች ባለቤትና ቫይረሱ ይዟቸው ሻል ካላቸው በኅላ ከሆስፒታል የወጡ ኢትዮጵያዊ እናት በስልክ ከነገሩኝ የተወሰደ]

በጣሊያን ፓርማ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው ማለፋ ታውቋል።
የዛሬ ሳምንት ማክሰኛ ዕለት ለአራት ቀናት ያህል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ያለፈው የ50 ዓመት ጎልማሳና የቢሮ ሰራተኛ የነበሩት ኢትዮጵያዊ አንዱ ናቸው።
እኚህ ኢትዮጵያዊ ባለትዳርና የሁለት ሴቶች አባት ሲሆኑ፣ ባለቤታቸውም በቫይረሱ ፖዘቲቭ ተብለው ለሁለት ቀናት ተኩል ያህል ቫይረሱን ለመከላከል በተዘጋጀው ልዩ ማቆያ የህክምና ክፍል ውስጥ፣ ህክምና ተከታትለው ወደቤታቸው በመሄድ ተጨማሪ ጥንቃቄና የህክምና ክትትል እንዲያደርጉ በህክምና ባለሞያዎች ተመክረው መመለሳቸውን፣ ከሰዓታት በፊት የደረሰባቸውን ሁነት በከባድ ሀዘን ውስጥ ሆነው በስልክ አስረድተውኛል።
የጉንፋን ምልክቱ፣ ምግብ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ድካም ትከሳት፣ ተደጋጋሚ ደረቅ ሳል፣ ….ወዘተ ለሰባትና ስምንት ቀናት ከባለቤታቸው ጋር ካጋጠማቸው በኅላ ወደሆስፒታል እንደሄዱ የገለጹልኝ እኚሁ በሀዘን ተጉጂ ኢትዮጵያዊ ወ/ሮ፣ ባለቤታቸው ህመም ጠንቶባቸው የጽኑ ህሙማን ማቆያ ክፍል (ICU) ውስጥ ገብተው በህክምና ቢረዱም በህይወት መትረፍ አለመቻላቸውን በእዝነት ነገረውኛል፣ የትዳር አጋራቸው የመተንፈሻ አካል ህመም (አስም) እንደነረባቸውም ይጠቅሳሉ።
ከባለቤታቸው ጋር ህይወታቸው ከማለፋ በፊት፣ አንደኛ ፎቅ እና ምድር ቤት ሆነው በስልክ ይነጋገሩ እንደነበረ በማስታወስም፣ እኔ ትንሽ ሻል ብሎኝ ከሆስፒታሉ ስወጣ ሃኪሞች ባለቤቴ ማረፋን ነግረውኛል ይላሉ። ሃኪሞች የቻሉትን ያህል እርዳታ እንደሚያደርጉ፣ የሰውን ህይወት ለማትረፍ ራሳቸውን መስዋዕት እስከ ማድረግ መድረሳቸውንም በበጎ ጎን ይጠቅሳሉ። ሆስፒታል የገባ ሁሉ አይሞትምም ባይ ናቸው።
ወደቤት ከተመለሱም በኅላ፣ የ18 እና የ16 ዓመት ሴት ልጆቻቸውም በቴክኖሎጂ መልዕክት ሳቢያ የአባታቸውን ማለፍ ማወቃቸውን አስረድተውኛል።
አያይዘውም፣ “አሁን ከቤት አንወጣም። ውጪውን በመስኮት ነው የምናየው። እኔም ሙሉ በሙሉ ነጻ ስባል ነው እኔም ልጆችም መውጣት የምንችለው። በቫይረሱ የሞተ ቤተሰብ ያላቸውና ታክመው ወደቤት የተመለሱ ሰዎች ክትትል ይደረግባቸዋል። ባለቤቴንም እስከአሁን አልቀበርነውም። በየዕለቱ ሰው ይሞታል። ቀብር ለሶስትና አራት ሰው ብቻ ነው የሚፈቀደው። የሚጠሩኝ ቀን እየጠበኩ እገኛለሁ። ማዘጋጃ ቤቱ ሟች በዝቶበታል። የሚሆነውን በሚዲያ እየተከታተልን ነው። ችግሩ ለሀገር፣ ለዓለም የመጣ ነው። የሀዘን ጨለማ ውስጥ ነው ያለነው። ያው የመጣውን ለመቻል ጥረት አደርጋለሁ ‘ ብለውኛል።
በማከልም፣ “ባለቤቴ የቢሮ ሰራተኛ ነው። በግል መኪና ነው ለስራ የሚመላለሰው። ከስራ ውጪ ብዙ ሰው የሚያገኝም አይደለም። ሱፐርማርኬት በመሄድ አስፈላጊ ነገሮችን ይገዛ ነበር። እኔ ግን በአውቶቡስ ነበር የምጠቀመው። በማን በኩል እንዴት ቫይረሱ እንደያዘን አናውቅም። አንዳንዴ፣ እኔ አውቶቡስ ስለምጠቀም አምጥቼበት ይሆን? ብዬ አስባለሁ። ግን እንዴት እንዴት እንደያዘን አላውቀውም። ህክምና ቦታ ሳንሄድ ከአንድ ሳምንት በላይ መቆየታችንም የጎዳን ይመስለኛል። ሰዎች በቻሉት ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው” በማለትም ይመክራሉ።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ከኢትዮጵያ በቅርቡ ልጆቻቸው ጋር ጣሊያን የሄዱ አንድ ኢትዮጵያዊ እናትም ሰሞኑን እንደጉንፋን አድርጎ የጀመራቸው ህመም፣ የኮሮና ቫይረስ ሆኖ በመገኘት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከትናንት በስትያ ማረፋቸው ተሰምቷል።
በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያጡ ሰዎችንና ኢትዮጵያዊ ወገኖችን ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር። የሟች ቤተሰቦችንም መጽናናትን ይስጣቸው።

ኤሊያስ ገብሩ

መንግስት በ ወለጋ ላይ የጣለውን አስቸኳይ ከዋጅ ያንሳ ። ኢንተርኔት የ ስልክ ግንኙነት ተቋርጧል ስለ ኮሮናም መረጃ እንዳያገኙ ሆነዋል

መንግስት በ ወለጋ ላይ የጣለውን አስቸኳይ ከዋጅ ያንሳ ። ኢንተርኔት የ ስልክ ግንኙነት ተቋርጧል ስለ ኮሮናም መረጃ እንዳያገኙ ሆነዋል ሲሉ ለ ሀበሻዊክሊ ምሬታቸውን ገለፁ በመሆኑም በ ኦሮሚያ የ ሀኪሞች ማህበር ባወጣው መግለጫ የ ኢንተርኔት እና የ ስልክ አገልግሎት እንዲከፈት ጠይቀዋል

ከ 3 ወር በፊት የታገቱት የ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ ተገደሉም ከሆነ መረጃው ለ ቤተሰብ መድረስ አለበት ሲሉ ለ ሀበሻዊክሊ ገለፁ

ከ 3 ወር በፊት የታገቱት የ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ ተገደሉም መረጃው ለ ቤተሰብ መድረስ አለበት ሲሉ ለ ሀበሻዊክሊ ገለፁ ተማሪዎቹ የውሃ ሽታ ሆነዋል ቤተሰብ ማልቀሳቸውን ቀጥለዋል ሃላፊነት የማይሰማቸው የ መንግስት አካላት ጉዳዉን በዝምታ ማለፍ መርጠዋል ሲሉ ለ ሀበሻዊክሊ ሃሳባቸዉን አጋርተዋል

ከነገ መጋቢት 9/ 2012 ዓ/ም ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ስጋት ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎቹን ሰርዟል።

EthiopianAirlines

http://www.fidelpost.com (ፊደል ፖስት) የተሰኘው የመረጃ ማሰራጫ ከታማኝ ምንጮች ነው መረጃውን ያገኘሁት ብሎ እንደዘገበው ከነገ መጋቢት 9/ 2012 ዓ/ም ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ስጋት ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎቹን ሰርዟል።

አየር መንገዱ ወደ ሱዳን [ካርቱም]፣ ግብፅ [ካይሮ]፣ ሊባኖስ [ቤሩት]፣ ፈረንሳይ [ፓሪስ] ፣ ኬንያ [ናይሮቢ እና ሞምባሳ] እንዲሁም ኳታር [ዶሀ] የሚያደርገውን በረራ ነው ላልተወሰነ ጊዜ የሰረዘው። የዱባይ እና የሌሎች ሀገራትንም በረራ ሊሰርዝ ይችላል ሲልም ድረገፁ አስነብቧል።

Design a site like this with WordPress.com
Get started