በኢትዮጵያ ስድስተኛው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተገኘ

በኢትዮጵያ ስድስተኛው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተገኘ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 8፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ስድስተኛው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ ውስጥ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሆስፒታሎች እና ከሆቴሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህ መሰረትም መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የመጣች የ 59 ዓመት የብሪታኒያ ዜግነት ያላት ዲፕሎማት ከሆቴል በተደረገ ጥቆማ በምትገኝበት እራሷን አግልላ እንድትቆይ መደረጉን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ዲፕሎማቷ በዛሬው ዕለት በተደረገላት የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዟ መረጋገጡን ነው ዶክተር ሊያ ያስታወቁት።
ከግለሰቧ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየትና የክትትል ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት ግለሰቧ በለይቶ የህክምና መስጫ ማዕከል የቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላት መሆኑ ተገልጿል።
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጰያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በፍጥነት ለይቶ እርምጃ ለመውሰድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
ህብረተሰቡም ይህንን አውቆ በሁኔታዎች ሳይደናገጥ በተረጋጋ መንፈስ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

FBC

የባልደራስ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ሰሞኑን የመሰረት ድንጋይ በተጣለበት መገናኛ 24/ አርሴማ ቤተክርስቲያን በመገኘት በግላቸው የ1ሺህ ብር ድጋፍ አደርገዋል

..”መልካም ተግባር
የባልደራስ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ሰሞኑን የመሰረት ድንጋይ በተጣለበት መገናኛ 24/ አርሴማ ቤተክርስቲያን በመገኘት በግላቸው የ1ሺህ ብር ድጋፍ አደርገዋል። አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለቤተክርስቲያኗ መልሶ ግንባታ የጉልበት ስራ በመስራት ያገለገሉ ሲሆን በነዋሪዉ በተደረገላቸው ጥሪ ቦታው ላይ በመገኘት በቻሉት ሁሉ የድጋፍ እርዳታ ማበርከታቸው ያካባቢውን ወጣት እንዳስደሰተ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ያዕቆብ ዳንኤል የተባለ የአዲስ አበባ ወጣት መገናኛ 24/ አርሴማ ቤተክርስቲያን አጠገብ የሚኖር በወቅቱ ቤተክርስቲያኗ አትፈርስም በማለት በኦሮሚያ ልዩ ሃይል ቶክስ በጥይት ከተመቱ ሰዎች መሀል አንዱ ነበር። ወጣት ያዕቆብ ዳንኤል ጉልበቱን ከተመታ ጀምሮ ከፍተኛ እንግልት እና ስቃይ ማሳለፉ የሚታወቅ ነው።
ዛሬ የባልደራስ አመራር ወደ አርሴማ ጎራ ባሉበት አጋጣሚ በሰፈር ሰዎች ጥቆማ ወደ ያዕቆብ ዳንኤል መኖሪያ ቤት በመሄድ ወጣቱን በመጎብኘት ጠይቀዋል። ወጣት ያዕቆብ ዳንኤል በጸጥታ ሃይል የደረሰበት አስነዋሪ ድርጊት ከአንደበቱ ሲናገር ለመታዘብ ተችሏል። ሙሉዉን ዝርዝር ከመረጃ ቲቪ ይከታተሉ። ይህን ወጣት በህክምና ለማገዝ የምትፈልጉ ሰዎች በውስጥ መስመር አድራሻውን መስጠት ይቻላል።

ምንጭ ስንታየው ቸኮል

በ ምዕራብ ኦሮሚያ ለ ወራት ተቋርጦ የቆየው የ ቴሌኮም አገልግሎት እንዲከፈት ቢጠይቅም መንግስት ችላ ብሎ አልፎታል

በምዕራብ ኦሮሚያ ለወራት ተቋርጦ የቆየው የቴሌኮም አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ክስተት ጋር በተያያዘ እንዲከፈት እየቀረበ ባለው ጥያቄ ዙሪያ እስካሁን የተለየ ነገር እንደሌለ የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ለቢቢሲ ገለጹ። https://t.co/07NwzsAAYv

በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የምድረ ገነት (አብደራፊ) ከተማ ከንቲባ በስራ ፈላጊ ሴት ላይ ጾታዊ ትንኮሳ በመፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ስጋት መለስ ስንል በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የምድረ ገነት (አብደራፊ) ከተማ ከንቲባ በስራ ፈላጊ ሴት ላይ ጾታዊ ትንኮሳ በመፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የምድረ ገነት ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ደረሰ አዱኛ በውሀ ተቋም ውስጥ ለመቀጠር ጥረት እያደረገች ካለች ስራ ፈላጊ ወጣት ጋር መጋቢት 5/2012 ምሽት 2:30 ሰዓት አካባቢ በሆቴል አልጋ ይዘው ከተኙበት በፖሊስ በቁጥጥር የዋሉ መሆናቸው ተገልጧል።አሚማ

source Ethiopia live updates

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቾች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ 15 ቀናት ይዘጋሉ ተባለ

ሰበር ዜና!

ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ኤፍቢሲ

በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ወደ ማቆያ ቦታ በመውሰድ ላይ ሳለ አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠው ግለሰብ በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዋለ

በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ወደ ማቆያ ቦታ በመውሰድ ላይ ሳለ አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠው ግለሰብ በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፌዴራል እና ከለጋምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እንዲሁም የፀጥታ መቃቅሩ የጋር ትብብር ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

ግለሰቡ በለጋምቦ ወረዳ 07 ቀበሌ ሰላም በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት ከሀገር ውጭ የወጣና አሁን የተመለሰ ነው፡፡

የለጋምቦ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት አበባው እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ ከውጭ ሀገር ተመልሶ አዲስ አበባ ሲደርስ የበሽታው ምልክቶች ታይተውበት ወደ ምርምራ በመወሰድ ላይ እያለ አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ በትናንትናው እለት ደሴ ከተማ ያደረ ሲሆን ዛሬ ጧት በሳይንት አጅባር አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተሳፍሮ ገነቴ ከተማ ለመድረስ ከአራት ኪሎ ሜትር ያልበለጠ ጎዞ ሲቀረው ወለቃ ወንዝ ላይ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ ጌትነት አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ Legambo communication

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ጠዋት ከጃክ ማ ጋር በአፍሪካ የCOVID19ን ስርጭት ለመግታት በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን ይፋ አድርገዋል።

COVID19

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ጠዋት ከጃክ ማ ጋር በአፍሪካ የCOVID19ን ስርጭት ለመግታት በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን ይፋ አድርገዋል።

ጃክ ማ ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ኮሮናን መመርመሪያ ኪቶችን እና 100 ሺህ ማስኮችን ለማሰራጨት ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር በመምረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድንቀዋል።

የሚደረገው ድጋፍ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን ለመንከባከብ የሚያስችሉ መመሪያዎችን አካትተው በቅርቡ የተዘጋጁ መጽሐፎችን ይጨምራልም ብለዋል።

ለ እረጅም ጊዜ እጣ ወጦላቸው ያልተላለፉ የ 20/80*የ ኮንዶሚኔም ቤቶች ለ እድለኞች እንዲተላለፉ እና ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደረገላቸው

በ13ኛው ዙር የ20/80 የኮንዶሚኒየም ዕጣ የደረሳቸው ዕድለኞች ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደረገላቸው
.
ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለ13ኛ ጊዜ ዕጣ የወጣባቸውና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የደረሳቸው ዕድለኞች፣ በየወረዳቸው ቀርበው ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደረገላቸው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማትና አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ባስተላለፈው መመርያ መሠረት፣ ክፍላተ ከተሞቹ ከዕድለኞቹ ጋር ውል እንዲዋዋሉ ለወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች መመርያውን አስተላልፈዋል፡፡
ከክፍላተ ከተሞቹ መመርያ የተላለፈላቸው የወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች፣ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ውል ለመዋዋል ወደ ጽሕፈት ቤቶቹ ሲሄዱ ማሟላት የሚገባቸውን መሥፈርቶች በዝርዝር አሳውቀዋል፡፡
በመሆኑም ዕጣው የደረሳቸው ዕድለኞች የታደሰ መታወቂያ፣ ያገባ(ች) ከሆኑ የጋብቻ ሰርተፊኬት፣ ባልና ሚስት ከሚኖሩበት ወረዳ በስማቸው የግልም ሆነ የመንግሥት ቤት እንዳላቸው ወይም እንደሌላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡
ያላገባ(ች) ከሆነ በስድስት ወራት ውስጥ የታደሰ ሰርተፊኬት፣ የባንክ ደብተር፣ የተመዘገበው ዕድለኛ ከሌለ(ች) ሕጋዊ ውክልና ያለው(ላት) መሆን እንዳለበትም ተገልጿል፡፡ ከላይ የተጠቀሱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ዕድለኞች፣ ከክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ቅጽ 09 በመያዝና ዝርዝር ማስረጃዎቹን ፎቶ ኮፒ ይዘው በየወረዳቸው በመቅረብ፣ መዋዋል የሚችሉ መሆኑን ወረዳዎች አስታውቀዋል፡፡
የ13ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣው የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. መሆኑ ይታወሳል፡፡ ዕጣው በወጣ ማግሥት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በተለይ በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተገነቡበት ኮዬ ፈጬ አካባቢ በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት፣ የዕጣው ዕድለኞች ሳይዋዋሉ እስካሁን ቆይተዋል፡፡
መንግሥትም ጉዳዩ ከወሰን ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ለማጣራት፣ ከከተማ አስተዳደሩና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ ኮሚቴ በማዋቀር አስጠንቷል፡፡ በውጤቱም ዘጠኝ ሺሕ ቤቶች የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መሆኑን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡
ምንም እንኳን የኮሚቴው ጥናት ውጤት ለሕዝብ ይፋ ባይደረግም፣ ከዓመት ቆይታ በኋላ ዕጣ የደረሳቸው ዕድለኞች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ተዋውለው፣ ቀጣይ የማስተዳደር ሒደት በክልሉ ሥር ሊሆን እንደሚችል መገለጹን በረቡዕ ዕትም መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ውል ማዋዋል በየወረዳው መጀመሩም ተጠቁሟል፡፡
15 March 2020
ታምሩ ጽጌ
ሪፖርተር

ተፅኖ ፈጣሪው ፖለቲከኛ እስክንድር ነገ ትናንት የተደረገውን የ ፕልፅግና ፓርቲ የ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አስመልክቶ ተከታዉን መልክት በ ትዊተር ገፁ አስፍሯል

ኢህአዴግ/ብልፅግና ገንዘብ አልሰበሰበም አስፈራርቶ ገንዘብ ቀማ እንጂ ፈረንጆቹ ይሄን extortion ይሉታል ገንዘቡ ግን በ አዲስ አበባ አንድ ወንበር (በ ፌደራሉ ፓርላማ ) አያስገኝለትም !! ድል ለ ዲሞክራሲ !

ተፅኖ ፈጣሪው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ ከ 17 አመት በፊት ተማሪ እያለ በ ሲንጋፖር ካምቦዲያ የነበረውን ስርአት በዚ መልኩ ያስታውሳል 👇

የዛሬ አስራ ሰባት ዓመት አካባቢ ስኮላርሺፕ አግኝቼ መጀመሪያ ወደ ሲንጋፖር ነበር ያቀናኹት፡፡ በአንድ የግማሽ መንፈቀ-ዓመት እርፍት ወቅት ከሲንጋፖር አቅራቢያ የምትገኘውን ካምቦዲያ የምትባል ሀገር ልጎበኝ ሄድኹ። እኔ ወደዚያ ያቀናሁት የዕረፍት ጊዜዬን እነዚያ ስመ-ገናና የአንኮር መስህቦችን ለማየት ነበር። እግረ መንገዴን ግን ሀገሪቷ ያለፈችበትና እስከአሁንም ድረስ ሰቆቃው ያልደበዘዘውን ዘግናኝ የጭፍጨፋ ታሪክ ሰማኹ። ጭፍጨፋ የተካኼደባቸውንና ዜጎች በጅምላ የተቀበሩባቸውን ስፍራዎች በሕይወት በተረፉ ሰዎች ተራኪነት ጎበኘሁ። ታሪኩ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው … በ1975 እ.ኤ.አ ፖል ፖት በሚባል ሰው የሚመራው የኻሜር ሩዥ ቡድን በካምቦዲያ ሥልጣን ተቆጣጠረ። ቡድኑ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ከምሁራን፣ መምህራን፣ ተቃዋሚዎች ወዘተ የሚቀርብበት ትችት ላሰበው ‹‹አብዮት›› ጸር እንደኾነ ተገነዘበ። ይህን ትችት ለምቋቋም እና ሥልጣኑን ለማጠናከርም የተማረውን ክፍል ከማጣጣል አልፎ የሀገሪቱ ችግሮች ሁሉ ምንጭ አድርጎ መፈረጀ ጀመረ። ምሁሩን እንደ ጸረ አብዮት፣ ችግርን መተንተን እንጂ መፍትሄ መሻት የማይችል፣ መንግሥትን ከመተቸት አልፎ ማገዝ የማይፈልግ የሰነፍ ቅምጥል፣ የውጪ ኋይል ተላላኪ፣ ከተፈጥሮ ጋር ታግሎ የሚኖረው ገበሬ ተለጣፊ ወዘተ በማለት በመንግሥት ሚዲያ ዘመቱበት፡፡ ካድሬውም የስም-ማጥፋት ዘመቻውን አጧጧፈው። ይባስ ብሎ የኻሜር ሩዥ ቡድን አባላት ልሂቃኑ ካልተወገዱ ‹‹አብዮቱ›› ግቡን አይመታም ወደሚል መደምደሚያ ተሸጋገሩ።
በውሳኔው መሠረት ሕዝቡን ከምሁሩ ተጽዕኖ የማጽዳት ዘመቻ ተጀመረ። መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ reeducation camp (እንደ እኛ ሀገሮቹ ጦላይ፣ ብር-ሸለቆ ካምፖች ማለት ነው) ተወስደው ተረሸኑ። እድለኛ የኾኑት ገበሬ ኾነው የእርሻ መሬት እንዲያርሱ ተደረገ። ዩኒቨርሲቲዎች የቆሻሻ ሐሳብ ማፍለቂያ ተብለው ( litertally) ወደ እንሰሳት ማርቢያና በረት ተቀየሩ። የማጽዳት ዘመቻው በምሁራን ብቻ አላበቃም።
የከተማው ሕዝብ በምሁራኑ ጸረ-አብዮት አመላካከት እና የኑሮ ዘይቤ ተበክሏል ስለተባላ ከተሞችን ባዶ ያደረገ የማፈናቀል ዘመቻ ተካኼደ። ከጅምላ ርሸናው የተረፈው ከተሜ ወደ ገጠር በገፍ ተግዞ የእርሻ ‹‹አብዮት›› እንዲያካሂድ ግዳጅ ተጣለበት፡፡ የምሁራኑ መወገድና የከተሞች መራቆት ኢኮኖሚውን በእንፉቅቅ አስኬደው። ረሃብ ሰተት ብሎ ለመግባት ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ ከጥይት ርሸና የተረፈው በረሃብ አለቀ። በዚህ መልኩ የኻሜር ሩዥ አምባገነናዊ ቡድን በሥልጣን በቆየበት 4 አጭር ዓመታት (1975-1979) እስከ 2.5 ሚሊዮን የሚጠጋ (የሀገሪቱን 25%) ሕዝብ ለሞት ዳረገ።
የጠ/ሚነስትር ዐብይ አሕመድ የትናንት ምሁራዊትን የሚያጣጥልና ለማሸማቀቅ ረዥም ርቀት የተጓዘው ንግግር በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ በደብዛዛው ሲታይ የነበረውን ጸረ-ምሁራዊነት አዝማሚያ ገሀድ ያወጣ ክስተት ኾኖ ተመዘግቦ አልፏል፡፡ ጸረ-ምሁርነት (anti-intellectuali
sm) ማለትም ፖሊቲከኞች የሚያራምዱት የልሂቃንና ምሁራን ጥላቻ እና ፍራቻ የሀገርን ዓይን አጥፍቶ የሚያሳውር አደገኛ አመለካከት ነው። ምሁርነት እና ምሁራንን ማጣጣል ብሎም ማጥላላት በትንሹ ማኅበረሰቡ በተለይ ታዳጊ ሕጻናት እና ወጣቶች ለትምህርት እና እውቀት ያላቸው ክብር እና ምኞት እንዲቀንስ ያደርጋል። ባስ ሲል ደግሞ ከላይ እንዳየነው የምሁራን ፍጅት እና የሀገርን መድቀቅ ሊያስከትል ይችላል።
ካምቦዲያን እንደ ምሳሌ አነሳን እንጂ ስፔን፣ አርጀንቲና አንዲሁም ጣሊያን ላይ ነግሰው የነበሩ አምባገኖች ጸረ-ምሁር ዘመቻ በማካሄድ ሺዎችን ገድለዋል። ጸረ-ምሁርነትን የሚሰብኩ ገዢዎች ብዙውን ጊዜ መዳረሻቸው ፋሺስታዊ አምባገንን መኾን ነው። ወደ ሀገራችን ስንመለስ ደርግ ምሁራኑ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ማስታወስ ይቻላል። የደርግ ቀይ-ሽብር ዘመቻ ተመሳሳይ አዝማሚያ የነበረውና ብሩህ አእምሮ የነበረውን አንድ የሀገራችንን ትውልድ የፈጀ ነው፡፡
ለኢሕአዴግም ጸረ-ምሁርነት አዲስ አይደለም። ትዝ ይለኛል የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ አንድ ያነበብኳት የኢሕዴግ/ኦሕዴድ ቢጫ መጽሐፍ ‘Hayyonni gurguddoon farra dimokraasiifi misoomati’ (ትላልቅ ምሁራን ጸረ ዲሞክራሲ እና ጸረ ልማት ናቸው) ትል እንደነበር አስታውሳለሁ። ባለፉት ሁለት ዓመታት የመንግሥት ባለሥልጣናት አካባቢ ስናየው የነበረው ምሁርነትን የማጣጣል ዝንባሌ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሶ ዛሬ እዚህ ደረጃ ደርሷል፡፡ አሁን ደግሞ በግልጽ በሕዝባዊ መድረክና በቴሌቪዥን መቅረብ ጀምሯል።
በግሌ ይህ አካሄድ ሳይዘገይ እና ሳይከፋ ሊተች እና ሊታረም እንደሚገባው ይሰማኛል። እዚህ ላይ ምሁሩ አይተች ማለቴ አይደለም። ምሁሩ መተቸትና መነቀፍ አለበት። ምሁራኑ intelecual arrogance (ምሁራዊ እብሪት) እና elitism (እኛ ብቻ የተሻልን ነን) ዓይነት የአመለካከት ችግር ስላለባቸው በወጉ ሊነቀፉና ሊኼየሱ ይገባል፡፡ ነገር ግን በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ደረጃ በተደጋጋሚ ምሁርነትን የሚያራክስና የሚያጥላላ ንግግር፤ በተለይ በሽግግር ወቅት ሲደረግ ውሎ አድሮ ወደ መንግሥት አቋምነት እያደገ ኼዶ መንግሥት እና ምሁራኑን ወደ ባላንጣነት የሚያሸጋግር መዘዙም ፋሺስታዊ አምባገነንነት እና የምሁራን ፍጅት ሊኾን ይችላል። ሳይቃጠል በቅጥል።

Design a site like this with WordPress.com
Get started