አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ልብ የሚነካ አቤቱታ!
ክቡር ፍርድ ቤት፤ ለመጀመሪያ ቀን በዚህ ችሎት ላይ ስገኝ ከችሎቱ ጀርባ የተፃፈውንና “ተልዕኳችን የህግ የበላይነትን በማስከበር አርዓያ መሆን ነው ” የሚለውን ሳነብ እና ከአሁን ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ ተከስሼ ነፃ ያወጡኝ ፍርድ ቤቶች በመሆናቸው እውነተኛ ፍትህ ከዚህ ችሎት አገኛለሁ ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ዛሬ ግን በዚህ ችሎት ፊት የተገኘሁት ህጋዊ ግዴታዬን ለመወጣትና ለችሎቱ ያለኝን አክብሮት ለመግለፅ እንጂ ፍትህ አገኛለሁ ብዬ ተስፋ በማድረግ አይደለም፡፡ ክቡር ፍርድ ቤት፤ ይህንን ማለት የተገደድኩት በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡
1ኛ. ለፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጠው በምርመራ ሂደቱ ላይ ያሉት ለውጦች በዳኞች እየተመዘኑ ቢሆንም እስካሁን በቀረብኩባቸው አራት ችሎቶች ጉዳዩን ያዩት አራት የተለያዩ ዳኞች በመሆናቸው ምንም ዓይነት የምርመራ ውጤት ለውጥ በሌለበት ሁኔታ ተከታታይ የጊዜ ቀጠሮ እየተሰጠብኝ ያለው ከህጉ መንፈስ ውጭ በመሆኑ፣
2ኛ- ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ቀጠሮ እንዳለኝ፣ በአሁኑ ወቅትም ከፍተኛ የልብ ህመም ታማሚ እንደሆንኩ፣ ከህመሜ ጋር በተያያዘም በኮቪድ 19 ቫይረስ ብጠቃ ህይወቴ አደጋ ውስጥ ሊዎድቅ እንደሚችል የህክምና መረጃ አቅርቤ እያለና በፖሊስ የቀረበብኝ ክስ የዋስትና መብት የማያስከለክል ሆኖ እያለ ያለ አግባብ የዋስ መብት ተከልክያለሁ፡፡ ክቡር ፍርድ ቤት ከምገኝበት አሳሳቢ የጤና ችግር በእስር ላይ ከምገኝበት ለኮሮና እጅግ ተጋላጭ የሆነ እስር ቤት አንፃር የተከለከልኩት የዋስትና መብት ሳይሆን የሰው ልጅ መሰረቴዊ መብት የሆነውን በህይወት የመኖር መብቴን ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው ገና ወንጀለኛ ተብዬ ሳይፈረድብኝ የሞት ፍርድ እንደተፈረደብኝ መሆኔን ነው፣
3ኛ- በዚኅ በተከበረው ፍርድ ቤት ፊት አሁን እየተከራከርን ያለነው አንድ መንግስት እና አንድ ዜጋ አይደለንም፡፡ በህጉ መሰረት ከሳሽና ተከሳሽ ነን፡፡ ክቡር ፍርድ ቤቱ ለከሳሽና ለተከሳሽ መብት መከበር እኩል መቆም ሲገባው ሁል ጊዜ የከሳሽን ምክንያታዊ ያልሆነ ጥያቄ እየተቀበለ፣ በተቃራኒው ደግሞ የእኔን በመረጃ የተደገፈ ጥያቄ ውድቅ እያደረገ አድሏዊነት እየፈፀመብኝ በመሆኑ፣
4ኛ- በአጠቃላይ በአገር ደረጃ ያለውን ሁኔታ ስናይም ፍትህ እየተሰጠ ያለው ከችሎት አደባባይ ሳይሆን ከ4ኪሎ ቤተ-መንግስት መሆኑን እያየን ነው፡፡ በወቅቱ የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት በእስር ላይ የምንገኘው ዜጎች በብዙ ሺዎች የምንቆጠር ሆኖ እያለ፣ ልክ ሁላችንም አንድ ዓይነት ወንጀል እንደሰራንና ጉዳያችን በአንድ ዳኛና ችሎት ብቻ እየታየ እንደሆነ ሁላችንም የዋስ መብት ተነፍገን በተደራራቢ የጊዜ ቀጠሮ መብታችን በጅምላ እየተጣሰ ነው፡፡ ክቡር ፍርድ ቤት፣ እኛ ፍትህ የምንጠብቀ ው ከፍርድ ቤት እንጂ ከሳሻችን ከሆነው የ4ኪሎ መንግስት አይደለም፡፡ የ4ኪሎ መንግስት ሃላፊነት ህግ ማስፈፀም ነው እንጂ ህግ መተርጎም አይደለም፡፡ ክብር ፍርድ ቤት፣ በአጠቃላይ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው አራት ነጥቦች የሚያሳዩት የህግ ሳይሆን የፖለቲካ እስረኞች መሆናችንን ነው፡፡ አሁን በመጨረሻ ፖሊስ ” የሽግግር መንግስት ጥያቄ በማቅረብ መንግስትን የመገልበጥ ሙከራ አድርጓል ” በሚል ክስ ሲያቀርብብኝ መታየቱ ይህንን የሚያረጋግጥ ነው። በዚህ ሁኔታ እውነተኛ ፍትህ ይገኛል ብዬ ስለማልጠብቅ በጊዜ ቀጠሮ እየተመላለስኩ እኔና ጠበቃዬ አጉል ከምንጉላላ፣ ውድ የሆነው የፖሊስ እና የፍርድ ቤት ጊዜም ያለ አግባብ ከሚባክን- መቋጫ የሌለው የፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ እንዲቋረጥና ጉዳዩ የፖለቲካ ውሳኔ ሲሰጠውና ፖሊስ ” ምርመራዬን ጨርሻለው ” ባለ ጊዜ ከእስር ቤት ወደ ችሎት እንድቀርብ እንዲወሰን በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡ በዚህ የፍትህ ሂደት አቶ ልደቱ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ኢዴፓም ተስፋ የቆረጥን መሆኑን እና በእስር ቤት በሚደርስባቸው ማንኛውም አደጋ ተጠያቂው መንግስት እና መንግሰት ብቻ መሆናቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ በድጋሚ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ የታሰሩት አመራሮች ልደቱ አያሌው፣ኢንጂነር ይልቃል እና የባልደራስ አመራ ሮች እንዲፈቱ በድጋሚ እንጠይቃለን። ልደቱን ልታስሩ ትችሉ ይሆናል ለሃቅ እና ለእውነት ተቆርቋሪ የሆነውን ኢትዮጽያዊ አስተሳሰቡን ግን ከፓርቲው እና ከአባላቱ ማውጣት እንደማይቻል ወዳጅም ጠላትም ሊያውቁት ይገባል!
OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮም በተመሳሳይ የዋስትና የገንዘብ መጠን(10ሺህ ብር) ከእስር እንዲወጣ ተወሰነ
በሌላ መዝገብ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 18፤2012 የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
የቀረበው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ(OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮም በተመሳሳይ የዋስትና የገንዘብ መጠን(10ሺህ ብር) ከእስር እንዲወጣ ብይን መሰጠቱን ጠበቃ ከዲር ቡሎ ተናግረዋል።
አቶ ደጀኔ ጣፋ በዋስ ተፈቱ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አብረዋቸው በአንድ መዝገብ ችሎት የቀረቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ዛሬ ብይን ሰጠ።
ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ
ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠቱን ፓርቲው በዛሬው እለት አስታውቋል።
በዚህም መሰረት፡-
- አቶ መለስ አለሙ- የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
- አቶ ተስፋዬ በልጅጌ- በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
- ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ- በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የአለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ሆኖ ተመድበዋል።
FBC
ፕ/ር መረራ ያስነሱት አቧራና፣ ከፍተኛ አምባጓሮ የፈጠረው “የብሔራዊ ውይይት” ውሎ፣
ፕ/ር መረራ ያስነሱት አቧራና፣ ከፍተኛ አምባጓሮ የፈጠረው “የብሔራዊ ውይይት” ውሎ፣
(መሐመድ አሊ መሐመድ)
ነሀሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) አዳራሽ በተዘጋጀው “የብሔራዊ ውይይት” መድረክ ላይ እኛም ታድመን ነበር፡፡ በዚህ መድረክ አጨቃጫቂ ጽሁፍ ያቀረቡትን ፕ/ር መረራ ጉዲናን በሻይ ሠዓት አግኝቻቸው ባቀረቡት ጽሁፍ እጅግ መደንገጤን ገልጨላቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም ፕ/ር መረራ፣ በተለይ ለዶክትሬት (3ኛ ዲግሪ) መመረቂያቸው ” Ethiopia: competing ethnic nationalism and the quest for democracy, 1960-2000″ በሚል ርዕስ ባዘጋጁትና በመጽሐፍ መልክም ባሳተሙት የምርምር ሥራቸውና በሌሎችም ጽሁፎቻቸው አማካይ አቋሞችን በማራመድ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ፕ/ር መረራ ራሳቸው በዚህ መድረክ ባቀረቡት ጽሁፍ፣ “አሁን ለተፈጠሩት አለመግባባቶች መንስኤ የሆኑ ችግሮችን ነቅሶ ከማሳየት ባለፈ ሰፋ ባለ መልኩ ሚዛኑን የጠበቀ ነገር ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ አልተሰጠኝም” በሚል የመድረኩን አዘጋጆች ይወቅሳሉ፡፡
ነሃሴ 17/2012 ዓ/ም
@Hilina የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
Sidama
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 621 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 111 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- 91 ከሀዋሳ
- 8 ከማልጋ
- 3 ከአለታ ወንዶ ወረዳ
- 3 ከዳራ ወረዳ
- 3 ከአለታ ጩኮ ወረዳ
- 2 አለታ ወንዶ ከተማ
አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 1,128 በቫይረሱ የተያዙ
- 13 ሞት
- 281 ያገገሙ
AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ውስጥ በተደረገው 6,681 የላብራቶሪ ምርመራ 968 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ13 ሰዎች ሰዎች ህይወት አልፏል። (10 ከአስከሬን ምርመራ 3 ከጤና ተቋም)
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 138 ከንፋስ ስልክ ላፍቶ
- 133 ከአዲስ ከተማ
- 130 ከአራዳ
- 113 ከኮልፌ ቀራንዮ
- 106 ከጉለሌ ይገኙበታል።
SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,894 የላብራቶሪ ምርመራ 33 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- ከጋሞ 14 (6ቱ አርባ ምንጭ ከተማ፣ 5 ካምባ፣ 2 ከጋርዳማርታና 1 ከቦንኬ) ፣
- ከጎፋ 9 ( 9ኙም ከመሎ ወረዳ) ፣
- ከወላይታ 6 (4ቱ ከሶዶ ከተማ፣ 1 ከሶዶ ዙሪያና 1 ከኪንዶኮይሻ ወረዳዎች )፣
- ከካፋ 3 (3ቱም ከቦንጋ ከተማ) እና ከደራሼ 1 የተገኘባቸው ዞኖችና ወረዳዎች ናቸው፡፡
@tikvahethiopiaBOT
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን በዛሬው እለት የጣና እንቦጭ ማስወገጃ ማሽኖችን በመግዛት ለክልሉ መንግስት አበርክተዋል።የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በዚህ የተቀደሰ ተግባር ላይ ጊዜያችሁን ፤ጉልበታችሁንና፤ ገንዘባችሁን ሳትሰስቱ ላበረከታችሁ በውጭ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ኩራት ነው።የተደረገው ድጋፍ ከመጭው መስከረም ወር ጀምር የጣናን እንቦጭ በዘላቂ መንገድ ለመፍታት በፌዴራልና በክልሉ መንግስት የተያዘውን እቅድ የሚያጠናክር ድጋፍ ነው።”ስንተባበር የማንሻገረው አቀበት አይኖርም”
Fekadu Mahtemework to be released 💚💛❤
Update: Among the 4011 to be released is Fekadu Mahtemework, managing editor of the privately-owned weekly publication Ghion, was convicted of tax evasion and sentenced to seven years in prison and a fine of about $227 in October 2019. The charges date back to 2014, under # Ethiopia ’s previous administration, and were filed against Fekadu in connection to the now defunct Enku magazine and a publishing company owned by his brother.
Read his background via CPJ here: https://cpj.org/data/people/fekadu-mahtemework/index.php
Picture: Elias Gebru Godana
Addis standard
ረጅሙ ፋኖን ማስፈራሪያ መግለጫ ከ አማራ ብልፅግና ፓርቲ
ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ!!
የተከበራችሁ የጎንደር ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም በቅርብም በሩቅም ያላችሁ ወገኖቻችን፦
በአሁኑ ወቅት ከመሠረቱ እየተለወጠ ባለ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህንን ግምት ውስጥ ያስገባ ሀገራችን ኢትዮጵያም በዓይነቱ አዲስ የሆነ ሪፎርም በማካሄድ ላይ ናት፡፡ ምክንያቱም የተለየ ታክቲክ ተከትለን ሪፎርም አካሂደን መለወጥ ካልቻልን ልማት ማስቀጠልም ማህበራዊ ሠላማችንን ማስጠበቅ አንችልም፡፡
ሀገራዊ ሆነ ክልላዊና አካባቢያዊ ለውጡ ሁለት መልክ ያለው ሲሆን እጅግ የሚያማልል ተስፋን የጫረ በተቃራኒውም ከፊት ለፊታችን ፈተናችንን የሚያበዙ ተግዳሮቶችም አሉብን፡፡
ስለሆነም በሀገራችን፣ በክልላችን ብሎም በከተማችን ከቀውስ የሚያወጣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድሎቻችን የሚያሰፋ የሪፎርም ታክቲክና ስትራቴጅ ተነድፎ እየተተገበረ ነው፡፡
የከተማችንን ሁኔታ ስንመለከት ሀገራዊ ለውጡ ጥሎን እንዳይሄድ ወደ ኋላ ከተጎተትን ሌሎቹ ከደረሱበት መድረስ ስለሚያቅተን በድሮ ስም፣ ክብርና ዝና ብቻ የዘመኑን ፈተና ማለፍ ስለማንችል ለሀገርም ለአለምም አስደማሚ የሆነ ከድሮ አባቶቻችን ክብርና ዝናችንን የሚመጥን ሁለንተናዊ ሪፎርም ውስጥ መግባት ግድ ይለናል፡፡
የጎንደር ከተማ ሁኔታ ከሀገራዊ ሁኔታ የሚያመሳስላት በአንፃሩም ደግሞ የተለየ የሚያደርጋት ሁኔታዎች አሉ፡፡
የከተማችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መድከም፣ የደህንነት ቀውስና አለመረጋጋት እንዲሁም የሠላም መታጣት በከተማችን ያለ ያለፋት ወደ 400 የሚጠጉ ዓመታት ያካበትነው የከተማነት ታሪካችን በእጃችን ያለውን የከተማችን ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቶቻችን እያሳጣን ነው፡፡
በከተማችን የፀጥታ የሠላምና የደህንነት ችግሮች የከተማው ህዝቦች አንድነት አለመጠናከር እዚያው ሳለ የከተማዋን ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና የንግድ እንቅስቃሴ ክፋኛ በመጉዳቱ የዚህን ችግር ምክንያት ማወቅ፣ መተንተንና ከመላው የከተማችን መፃኢ እድል እያሳሰባቸው ካለ ወገኖች ጋር መቅርቡ መለየት፣ መግባባትና ለመፍትሄው መሯሯጥ የግድ የሚልበት ምክንያት ዋነኛ የወጣቱ የሥራ እድል መፍጠሪያ እና የኢኮኖሚ ምንጭ ወደ መንጠፍ አቅጣጫ እየሄዱ በመሆኑ ነው፡፡
ከምንም በላይ የከተማችን የሰላምና ደህንነት ሁኔታ ኢ-ተገማች በመሆኑና ያልተረጋጋ በመሆኑ መዋከቡ ሲበዛና የከተማ አስተዳደሩ አመራርና ህዝብ ባልሰከነ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ መሆኑ የከተማዋን የሰላም መታጣት ችግር የበለጠ እያወሳሰበው መምጣቱ ብቻ ሳይሆን ህገ ወጥነትና የጎበዝ አለቅነት እየተበራከተ እንዲመጣ አድርጓል፡፡
በዚህም የከተማችን ቅስም እስከወዲያኛው እንዲሰበር ለሚፈልጉ ለከተማው ክፋ የሚያስቡ ከውስጥም ከውጭም ያሉ ኃይሎች በሙሉ ምቹ ሁኔታ እየፈጠርን መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
የጎንደር ህዝብ አብዛኛው ወጣትና ትኩስ ሀይል ነው፡፡ ይህ የህ/ሰብ ክፍል የሥራ አጥነትና የኢኮኖሚ ችግር አለበት፣ በርካታ የጤናና ማህበራዊ ችግር እንዲሁም የከተማው የሠላምና የደህንነት መታጣት ችግር ይህንን የህ/ሰብ ክፍል የበለጠ ተጎጅ እያደረገው ነው፡፡
ስለሆነም የጎንደር ከተማ ህዝብ በተለይም ወጣቱ ቅድሚያ የከተማው ህግና ሥርዓት ሠላም የሰፈነበት በማድረጉ ሂደት መሪ ተዋናይ በመሆን ከተማዋ የኢንቨስትመንት የቱሪዝምና የንግድ ማዕከል እንድትሆን መስራት አለበት፡፡
የተከበራችሁ የከተማችን ህዝቦች በቅርብም በሩቅም ያላችሁ ወገኖቻችን
የአማራ ህዝብ እየታየ ያለውን ሀገራዊ ክልላዊ ለውጥ እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ታግሏል፣ ደም ገብሯል፡፡ የጎንደር ከተማ ህዝብም የመጀመሪያውን የለውጥ ችቦ በመለኮስ ግፍና በደል እንዲቆም፣ ፍትሃዊነት እንዲሰፍን፣ የማንነትና ወሰን ጥያቄዎች እንዲመለሱ የለውጡ ፋና ወጊነቱን ያስመሰከረ ህዝብ ነው፡፡
ለለውጡም መላው ህዝባችን ፋኖ ተሰማራ በሚል አኩሪ ገድል ፈፅሟል፡፡ አፋኙ ኃይል ወደ አንድ ጥግ እንዲገፋ አድርጓል፡፡ የክልላችን የለውጥ ሠራዊት የሆነው በክልሉ በተለይም በከተማችን ያለው ህዝባዊው ፋኖ ከለውጡ በኋላ መላ ቀልቡንና አቅሙን ወደ ልማት በማዞር ፀረ ድህነት ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በተጓዳኝም የመላው የለውጥ ሀዋሪያ የሆነው የአማራ ህዝብ የወል መጠሪያ የሆነውን ፋኖን በማንገብ በተገኘው አጋጣሚ በሙሉ የአማር ክልል ህዝቦች ጥቅም የሚጎዳ አመለካከትና ተግባርን በሰለጠነ አግባብ በሠላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት እየታገለ ይገኛል፡፡ እውነተኛው የፋኖ ንቅናቄ የመላው አማራ ክልል ህዝቦች የለውጥ ንቅናቄ መጠሪያ ሁኖ ለለውጡ ያበረከተው አስተዋጽኦ ማንም ደፍጥጦት የሚያልፍ ጉዳይ አይደለም፡፡
ነገር ግን አሁን በተለይም በከተማችን እየተፈፀመ ያለው ጉዳይ ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ፋኖነት በህዝብ አእምሮ ውስጥ ያለ በዋናነት የአማራ ክልል ህዝቦች አስተሳሰብ (Sentiment) ነው፡፡ ፋኖነት ህዝባዊነት ነው፡፡ ፋኖነት ለህዝብ ፍትህ፣ ለሠላም፣ ለልማት፣ ለአንድነት በአጠቃላይ ለተገፋ ህዝብ መቆምና መወገን ነው፡፡ ፋኖነት ለተጎዱ ላልተጠቀሙ ባይተዋርነት ለሚሰማቸው አጋር መከታ መሆን ነው፡፡ ፋኖነት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ ቋንቋ አይገድበውም፡፡ ፋኖነት የአድዋ፣ የማይጨው፣ የካራማራ፣ የ2008ቱ የጎንደር ህዝባዊ ማዕበል መጠሪያ ስም ነው፡፡
ፋኖነት ለተወሰነ ቡድን የተሰጠ ማዕረግ ወይም ሹመት አይደለም፡፡ ፋኖነት የህዝብ አጀንዳ ማስፈፀሚያ ህዝባዊ የማዕረግ ስም እንጅ በህዝብ ስም የሚምሉ እና የሚገዘቱ የጥቂት ህገወጥ ቡድኖች የግል ጥቅም ማካበቻ ወይም የኑሮ ዘይቤ አይደለም፡፡
ነገር ግን አሁን በከተማችን እየሆነ ያለው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በአካባቢያችን ከትክክለኛው ፋኖ አላማ ውጭ በህገወጥ መንገድ የተደራጁ የታጠቁ ኃይሎች የተደራጁበት የውሸት ምክንያት የተለየ ከመሆኑም በላይ ጥቅም ማግበስበስ ዓላማ አድርጎ የተሰበሰበ ኃይል ነው፡፡
በዚህ ህገወጥ ቡድን መደራጀት በአሁኑ ወቅት ለህዝብ መታገል ሳይሆን የኑሮ ዘይቤ የመተዳደሪያ ገቢ ማግኛ ዘዴ ሁኗል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ለትክክለኛ ህዝባዊ አላማ ለመታገል መስሏቸው ተደራጅተው የህገወጡ ቡድን አጠቃላይ አካሄድ የሚፈፅማቸው ፀያፍ ድርጊቶች አልጥማቸው ሲል ራሳቸውን ያገለሉ አካላትን አብነት አድርጎ ማንሳት ይቻላል፡፡
በከተማችን ያለው ከዋናው ፋኖ አላማ ውጭ በህገወጥ መንገድ በቡድን ተደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን በርካታ ህገ ወጥ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ለዚህም በቂ የሰው፣ የሰነድ፣ የኦዲዮ እና የቪዲዮ መረጃዎች አሉ፡፡ ከሚፈፅማቸው ህገ ወጥ ተግባራት መካከል ታጥቆና ተደራጅቶ በከተማው ይንቀሳቀሳል፣ ያለምንም ከልካይ ኬላ ጥሶ ከከተማ ይወጣል፣ ይገባል፣ ሰው ያግታል፣ ግድያ ይፈፅማል፣ ዘር ቆጥሮ የግለሰብ ቤት ነጥቆ ካምኘ ያደርጋል፣ ከባለሀብት በግዴታ ገንዘብ ይሰበስባል አንዳንዴም ይቀጣል፣ የከተማ መሬት ታጥቆ አጥሮ በመያዝ ቤት ይሰራል፣ በፖሊስ እጅ ያለ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ እስር ቤት ጥሶ ገብቶ ያስፈታል፣ ህግ ጥሶ የወረደን የጦር መሣሪያ ታጥቆ ፖሊስ ጣቢያ በመውረር ዘርፎ ያመጣል፣ አስከሬን አጅቦ በመምጣት ጎንደርን በቶክስ ይንጣል፣ መሸታ ቤት ገብቶ ጠጥቶ አልከፍልም ይላል፣ በተደጋጋሚ በልዩ ልዩ የከተማው አካባቢወች ጥይት ይተኩሳል፣ ታዋቂ ግለሰቦችን በቡድን ተደራጅቶ የቡድን መሳሪያ ጭምር ታጥቆ ያጅባል፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የመንግስት ተቋማትን፣ ፖርቲ ቢሮዎችን ይከባል፣ ያስፈራራል፣ አመራር ለመግደል እቅዶችን ያቅዳል፡፡
ይህ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን እያወቀ የክልሉ መንግስትና የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ኃይል በሰለጠነና በሠላማዊ መንገድ ያለ ደም መፋሰስ ከዚህ ህገ ወጥ ድርጊቱ ታቅቦ የመንግስት ተገዳዳሪ ኃይል ሳይሆን ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጦ ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅት አድርጓል፡፡
በተለይም የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ወደ ክልሉ የፀጥታ መዋቅር እንዲካተቱ፣ መተዳደሪያ የሌላቸው በከተማ ብድርና መስሪያና መሸጫ ቦታ እንዲያገኙ፣ በኢንቨስትመንት አካባቢዎች በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ደግሞ የእርሻ መሬት እንዲሰጣቸው፣ በቂ መተዳደሪያ ያላቸው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ በእነዚህ መፍትሄወች የማይስማማ ብቻ ለከተማችን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል መንግስት ህግን ለማስከበር እንደሚገደድ መፍትሄዎች አስቀምጧል፡፡
በእነዚህ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ከሚመለከታቸው ጋር ከቀናት በኋላ ከክልሉ ከፍተኛ አመራር ጋር ውይይት ለማካሄድ ዝግጅት ላይ በነበርንበት ጊዜ ሁሌም በህገወጥ መንገድ መቀጠል የሚፈልጉ የቡድኑ አባላት አዳዲስ ህገ ወጥ ድርጊቶችን ፈፀሙ፡፡
እነዚህን የመፍትሄ አማራጮች እያሳየንና ብዙወቹ ፈቃደኝነታቸውን እያሳዪ ባሉበት ሁኔታ የህገወጡ ቡድን አባላት ጎንደር ከተማ ላይ ሀሙስ መጋቢት 10/07/2012 ከቀኑ 11 ሰአት ከአራዳ ክፍለ ከተማ ብጥብጥና ሁከት በማስነሳት ከጀርባው በአካባቢው ባሉ የህገወጡ ቡድን ታጣቂዎች ታጅቦ የመኪና መንገድ በልዩ ልዩ ቁሳቁሶች እየዘጋ ልዩ ልዩ ፅንፈኛ መፎክሮችን እያሰማ ወደ ዞኑ ፖሊስ መምሪያ በመሄድ በህንፃውና በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የተሞከረ ሲሆን አመፁንም የከተማችን የፀጥታ ሀይል በፍጥነት ደርሶ በትኖታል፡፡
ይህ ምልክት ማምሻውን ተጨማሪ ሁከትና ብጥብጥ ለማቀጣጠልና ከተማዋን ወደ አጠቃላይ ቀውስ ለመውሰድ የሚደረግ ዝግጅት መኖሩን ያረጋገጠው የከተማችንና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጋራ ኮማንድ ፖስት የህዝባችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ተጨማሪ የፀጥታ መዋቅር በተመረጡ አካባቢዎች ስምሪት አደረገ፡፡
በዚሁ እለት ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ ማራኪ ክፍለ ከተማ ሽዋ ዳቦ አካባቢ በአካባቢው ሲያልፋ የነበሩ በአካባቢያችን የተሰማራ የመንግስት የፀጥታ ሀይል አባላት ላይ በተከፈተ ቶክስ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል፡፡
ይህ ታጥቆ ተደራጅቶ በፀጥታ ሀይላችን የህይወት መስዋትነት እየከፈለ በዚህ ህገወጥ ቡድን ተመሳሳይ አፀፋ መሰንዘር አልተፈለገም ነበር ይልቁንም የፀጣታ ሀይላችን የህዝብ ልጅ መሆኑንና ዳግም ህዝባዊነቱን ያስመሰከረበት አኩሪ ገድል ነበር፡፡
ይህንን ጉዳት ያደረሰው ህገወጡ ኃይል ይህንን ድርጊት ከፈፀመ በኋላ በህገወጥ መንገድ ወደመሸገባቸው ቦታወች ሸሽተው በመደበቃቸው የክልላችን የፀጥታ ሀይል አባላት የመሸገበትን አካባቢ በፍጥነት ለመቆጣጠርና ጥቃት አድራሹን ቡድን በቁጥጥር ሥራ ለማዋል ፈጥኖ ቦታዎችን ቢቆጣጠርም ቡድኑ ቶክስ ከፍቶ ከአካባቢው ተሰውሯል፡፡
የተከበራችሁ የከተማችን ህዝቦች በቅርብም በሩቅም ያላችሁ ወገኖቻችን
ችግሩ በዚህ ብቻ አላበቃም በሚቀጥሉት ቀናትም ህገ ወጥ ሰልፋ፣ ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ ከመሀል አገር አዲስ አበባ ድረስ የተላኩ በተሽከርካሪ የታገዘ የአድማ ወረቀት የመበተንና በህገወጥ መንገድ የተደራጀው ህገ ወጥ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም አልያም ቡድኑ ጉልበቱ እንደፈረጠመ የፈለገውን ህገ ወጥ ስራ እየሰራ መንግስትን እየተገዳደረ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ሌሎች ተላላኪ ኃይሎች በርካታ ጥረት አድርገዋል፡፡
ሁለቱም ድርጊቶች በሠላም ወዳዱ የጎንደር ህዝብና በፀጥታ መዋቅራችን የጋራ ጥረት አልተሳኩም፡፡ የጎንደር ህዝብ ልብ ሊል የሚገባው ጎንደር ቅስሟ እንዲሰበር በውስጥም በውጭም ያሉ ጠላቶቻችን ያለ የሌለ ሀይላቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡
የተከበራችሁ የከተማችን ህዝቦች በቅርብም በሩቅም ያላችሁ ወገኖቻችን
በህገወጥ መንገድ የተደራጀው ህገ ወጥ ቡድን ከመሸገበት አካባቢዎች እንዲለቅና እንዲበተን ከተደረገ በኋላ በዋናነት ሁለት ጎላ ጎላ ያሉ የህዝብ ስሜቶች በከተማችን ተፈጥረዋል፡፡
የመጀመሪያውና በርካታው የከተማችን ሆኑ በዙሪያው ያሉ ዞኖችና ወረዳዎች ህዝቦች በተወሠደው እርምጃ ከፍተኛ ደሰታ ተሠምቷቸዋል፡፡ ወደ ኃላ እንደትመለሱ ህግ አሰከብሩ፣ አጥፊን ጠይቁ ፣ከመንግሥት ጋር የሚገደደር ሀይል ይበተን፣ ሠላማችንና ደህንነታችንን መልሱልን ፣ የህዝባችን አንድነት አጠናክሩ፣ የሚል የጎሉ ሀሰቦች ተንፀባርቀዋል፡፡
በአንፃሩም ደግሞ ህገወጥ ቡድኑ እየፈፀመ ያለውን ድርጊት ትክክለኛ መረጃ ካለማግኘት በመነጨ መንግሥት የወሠደውን ህግ የማስከበር እርምጃ ፋኖን ለማጥፋት ነው የሚል የተዛባ ትርክት አልፎ አልፎ በግለሰብ ደረጃ እየተሠማ ሲሆን መንግሥት የተደከመ ስለሆነ ዋስትናችንና የቁርጥ ቀናችን ይህ ቡድን ነው በሚል መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃውን ለማጣጣል ከተቻለም ለማደናቀፍ የሚጥሩ ጥቂት የውስጥና የውጭ ተላላኪ ሀይሎች ተስተውለዋል፡፡
አሁን በተጨባጭ ያለው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥንካሬውን እያረጋገጠ እየመጣ መሆኑ እየታወቀ እንደተባለው የአፈፃፀም ድክመት እንኳን ቢኖር በህግ በስርዓት የማይመራ ቡድን የፈለገውን እያደረገ ይቀጥል ከማለት የመንግሥት ድክመት ፈልጎ ተጋግዞ ማረም በተገባ ነበር ፡፡
መላው ሠላም ወዳዱ የክልላችን ሆነ የጎንደር ከተማ ህዝብ በተቃራኒው ደግሞ ጥቂቶቹ ለጎንደር ወድቀት ሌት ከቀን የሚጥሩ ሀይሎች ሊገነዘቡት የሚገባ ሀቅ ቢኖር በከተማው አስተዳደር እሰከለ ድረስ በህገወጥ መንገድ ታጥቆ ተደራጅቶ ከነፍስ ወከፍ እሰከ የቡድን መሳሪያ አንግቦና ካምኘ መስርቶ መኖር አይቻልም፡፡
የክልላችን መንግሥት ሆነ የከተማችን አስተዳደር የታጠቀን ህገወጥ ቡድን አይታገስም ፣ ህግ ያሰከብራል፡፡ የክልላችን ሆነ የከተማችን የውሰጥም ሆነ የውጭ የፀጥታ ችግር የሚፈታው በክልላችን እና በፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች ብቻ እንጅ በሌላ በማንም ቡድን ሊሆን አይችልም፡፡
ስለሆነ የከተማችን ፀጥታ ችግር በባለቤትነት መፍታት ያለበት የከተማችን ህዝብና በተለይም ወጣቱ ከከተማችን ከክልላችንና ከፌደራል የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ነው ፡፡ ህዝባችን ሠላሙ የሚያረጋግጥለት ደግሞ የፀጥታ መዋቅራችን ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት እንጅ በሌላ በማንም ሀይል አይደለም፡የእስከአሁኑ ሂደታችንም በከተማችን ከሠላም ወዳዱ ህዝቦችን ጋር ተቀናጅቶ እየሠራው ያለው የፀጥታ መዋቅራችን የከተማችን የፀጥታ ሁኔታ በተለይም ዋና ዋና ወንጀሎች ትርጉም ባለው መልኩ እንዲቀንስ አድርጓል፣ ቀጣይም በእልህና በወኔ ሰላም የማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
የተከበራችሁ የከተማችን ህዝቦች በተለይም ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌወችና የሀይማኖት
ስለሆነም በቀጣይ የከተማ አስተዳዳራችን ከመላው የጎንደር ከተማ ሠላም ወዳድ ህዝብ ጋር በመሆን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡ በከተማችን የተጀመረውን ህግ እና ስርዓት የማስከበር ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ማንኛውም ቡድን ወይም ግለሠብ በከተማው ውሰጥ ታጥቆ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው ፡፡
ይህንን የክልሉ መንግሠት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ መመሪያ የጣሠ የያዘውን የጦር መሳሪያ አውርዶ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
በማንኛውም ሁኔታ ህግ በጣሰ መንገድ የሚካሄድ የጥይት ቶክስ የያዘውን የጣር መሳሪያ አወርዶ በወንጀልና በፍትህብሔር እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡
በከተማችን ህገወጥ ሠልፍ፣ የተዳከመውን የከተማችን ኢኮኖሚ ጭራሽ ይበልጥ እንዲዳከም ህገወጥ የሥራ ማቆም አድማ ለማካሄድ የሚቀሰቅስ፣ የሚያነሳሳ ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ መቆጠብ ያለበት ሲሆን ተባባሪ የሆነ ሁሉም በህግ ይጠየቃል፡፡
በህገወጥ መንገድ የተደራጀው ነገር ግን አሁን የተበተነው ህገወጥ ቡድን በሠላም እጁን ለመንግስት እሰከ መጋቢት 20/2012 እንዲሠጥ ይህንን አልፈፅምም ካለ ቡድኑን የመንግስት የፀጥታ ሀይል ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን የምናረጋግጥ ሲሆን ለዚህም ህዝባችን ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
መላው የከተማችን ህዝቦች በተለይም ወጣቶች አሁን የተፈጠረውን አንፃራዊ ሠላም እና እድል ወደ ዘላቂ ሠላምና ልማት እንዲቀየር በማድረግ ጎንደር የሠላም፣ የፍቅር ፣የአንድነት ፣የኢንቨስትመንት፣ የቱሪስት፣ እና የንግድ ከተማ እንድትሆንና ወደ ቀደመ ክብሯና ገናና ታሪኳ እንድትመለስ አብረን ሌት ከቀን እንድንሠራ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡
የከተማችን የክልላችንና የፌዴራል የፀጥታ መዋቅር የከተማችን ህዝብ ሠላሙ ዘላቂ እንደሆኑ እየከፈላችሁት ያለ መስዋትነት ታሪክ የማይዝነጋው መሆኑን አወቃችሁ አስተማማኝ ሠላም ሠፋኖ መላው የከተማችን ህዝብ በሙሉ ቀልቡ ወደ ልማት እስኪገባ ድረስ ሠላም የማስፈን ህግና ሥርዓት የማስከበር ህገወጥነትን የመከላከል ፣ አጥፊወችን ለህግ በማቅረብ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመሆን የህግ የበላይነትን እንድታረጋግጡ ጥሪያችን እናሳተላልፋለን ፡፡
በከተማችን ፣በክልላችን ሆነ በሀገራችን የምትገኙ ባለሀብቶች ሆናችሁ ዲያስፖራዎች ለከተማችን ልማት እያበረከታችሁ ያላችሁት አስተዋፅ እና ሁለንታዊ ድጋፍ ሁሌም እያደነቅን በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አላስፈላጊ ድርጊት ውስጥ ገብታችሁ የከተማዋን ችግር በማወሳሰብ የተጠመዳችሁ ጥቂት የውጭና የውስጥ ሀይላት ለጎንደር ህዝብ ስትሉ ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ አበክረን ማሳሰብ እንወዳለን፡፡
የከተማችን የመንግሥት ሠራተኞች ፣መምህራን፣ የህክምና ባለሙያወች በሙሉ በየተሠማራችሀብት መስክ ህዝብ በፍፁም ታማኝነት፣ከመድሎ ከሙስና በፀዳ መንገድ የአገልጋይነት መንፈስ እንድታገለግሉት የህዝብ ጥያቄ እንድትመልሱ የአደራ መልዕክታችን እናስተላልፈለን ፡፡
ከዚህም ሌላ በከተማችን፣ በሀገራችን ሆኑ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የምትገኙ የዲያስፖራ አባላት የማህበራዊ ሚዲያ እንቂወች /activist/ ብሎገሮችና የኮሚኒኬሸን ባለመያዎች ፣ነጋዴዎች፣አልሚ ባለሀብቶች ከከተማ አስተዳዳሩ ጋር በመሆን በቅርቡ በከተማችን ለልማት ምቹ ሁኔታ የሚፈጠር መሆኑን ስናበስራችሁ ለከተማችን የገፅታ ግንባታ እጅና ጓንት ሁነን እንድንሠራና ለጎንደር ትንሳኤ የበኩላችን አስተዋፅኦ እንድናበረክት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም መላው የከተማችን የሀይማኖት አባቶች እንደወትሯቹህ ከሀይማኖታዊ አስተምህሯቹሁና ከእምነት ተልኳችሁ አንፃር በተቃኘ አግባብ ሰላምን ልማትን አንድነትን ፍቅርንና መተሳሰብን እንድትሰብኩ የአደራ መልእክታችን እናደርሳለን፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
ተጨማሪ መረጃ የ ሮናልዲኖ ጎቾ በ ፓሯጋይ እስር ከ ገንዘብ ዝውውር ጋር ሊገናኝ ይችል ይሆን 💚💛❤

The Real Reason Behind Ronaldinho’s Arrest Revealed
Pius The Real Reason Behind Ronaldinho’s Arrest Revealed
There was an information that former Brazil and FC Barcelona superstar Ronaldinho was arrested for being in possession of a fake passport, it has now been claimed he might have been involved in something more serious.
The 39-year-old and his brother have been in jail for more than a week following their recent arrest after they were caught with fake Paraguay passports by Paraguayan authorities.
Ronaldinho and his sibling were then denied bail, which has seen the ex-superstar get used to life behind bars, with reports suggesting he could be detained for as long as six months while his case investigated.
This past weekend, the former AC Milan playmaker took even part in a futsal match in prison, during which he scored five goals and assisted six further strikes in an 11-2 victory.
Now, according to an ESPN report, there could be more to Ronaldinho’s case as there is a suspicion the 2002 FIFA World Cup winner is involved in a money laundering scheme with a Paraguayan businesswoman.
The former Selecao international was invited to the country by Dalia Lopez, who is believed to arrange the entire visit and met Ronaldinho and his brother at the airport they were arrested at.
The leading prosecutor in the case, Osmar Legal, said this explains why they have want to keep Ronaldinho in prison.
“She could be involved in a money laundering scheme and that means we have to investigate all the other people that were related to that kind of crime, including Ronaldinho,” he told Reuters.
“That is why we strictly maintain that he be kept in jail.
“Our major evident is that they produced false documents, that they used those documents (to enter Paraguay) and that they were eventually going to be used for some commercial means or investments which are not legal according to Paraguay government




