
በየአካባቢው ያልተቋረጡት ስብሰባዎች!
ዛሬ የተለያዩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፆችን ዞር ዞር እያልን እየተመለከትን ነበር። የብልፅግና ፓርቲ እንዲሁም ሌሎች ስብሰባዎችን እያረጉ እንደሆኑ ይገልፃሉ። በአንድ በኩል ህዝቡ ከመጠጋጋት እንዲቆጠብ መልዕክት እየተላለፈ፣ በሌላ በኩል መሰል ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት ስብሰባዎችን እየተመለከትን ነው።
Via TIKVAH-ETH
https://www.facebook.com/habeshaweeklytikusmereja/

በየአካባቢው ያልተቋረጡት ስብሰባዎች!
ዛሬ የተለያዩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፆችን ዞር ዞር እያልን እየተመለከትን ነበር። የብልፅግና ፓርቲ እንዲሁም ሌሎች ስብሰባዎችን እያረጉ እንደሆኑ ይገልፃሉ። በአንድ በኩል ህዝቡ ከመጠጋጋት እንዲቆጠብ መልዕክት እየተላለፈ፣ በሌላ በኩል መሰል ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት ስብሰባዎችን እየተመለከትን ነው።
Via TIKVAH-ETH

ተጨማሪ ሙሉ መረጃ እንደ ደረሰን የምናቀርብ ይሆናል
ፍራንክ ሪቤሪ በበጎ ተግባር !
ፈረንሳዊው የፊዮሬንቲና ተጫዋች ፍራንክ ሪቤሪ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በቫይረስ ተይዘው በፍሎረንስ ሆስፒታል ለሚገኙ ታማሚዎች 50,000 ዩሮ መለገሱን ታውቋል ::


ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን በ96 አመታቸው አርፈዋል!
ላለፉት 61 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጉት ከፍተኛ እንቅስቃሴ 60,000 ገደማ ኢትዮጵያውያን የፊስቱላ ህክምና ተደርጎላቸዋል።
ነፍስ ይማር፣ ታላቅ ሰው!
የ ኢትዮቴሌኮም ከሚሰጣቸው አገልግሎት የብድር * 810# እና የ ጥቅል አገልግሎት *999# እየሰራልን አይደለም ሲሉ ደንበኞች ለ ሀበሻዊክሊ ገለፀዋል ችግሩ ምን እንደሆነ ለመጠየቅ ተደጋጋሚ የ ስልክ ጥሪ ብናረግም ሊነሳልን አልቻለም ተጨማሪ መረጃ ካለ የምናደርስ ይሆናል

ግብፅ 14 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ መኖሩን ዘግባለች ይሄም በ ቫይረሱ የተያዙትን ቁጥር ወደ 210 አድርሶታል ከዚ ውስጥ 28 የሚሆኑት አገግመዉ ከ ህክምና ሲወጡ 6 የሚሆኑት ህየወታቸዉን አጥተዋል
Daily news egypt
Egypt reports 14 new #Coronavirus cases, raising the total to 210 cases, of whom 28 have recovered and discharged from quarantine hospitals (six deaths so far): Health Ministry (@mohpegypt) https://t.co/zOuapiIV7z

“ከቤታችሁ እንዳትወጡ!” – ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን
የቱርክ ፕሬዘዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የሀገሪቱ ዜጎች ለቀጣዮቹ 3 ሳምታት አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በፍፁም ከቤታቸው እንዳይወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል። ይህ ውሳኔ የተለፈው ማህበራዊ ግንኙነቶችን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ቸሩ ሳይዶ ማኔ
የሊቨርፑሉ ኮከብ ሳይዶ ማኔ በተደጋጋሚ ለሀገሩ ሴኔጋል እና ለተወለደበት ቄዬ ይሄን አደረግ…እርዳታ ለገሰ ሲባል ሰምተናል።
ዛሬ የሴኔጋል ዌብሳይቶች ይዘውት በውጡት ወሬ መሰረት ደግሞ ሀገሩ ሴኔጋል አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እንድትከላከል የሚረዳትን 45ሺ ይሮ ድጋፍ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።
ወዳጆቻችን እናንተም ሳሙና መግዛት ለማይችሉት ግዙላቸው ። ህመሙን እንዴት መከላከል እንዳለባቸው በቂ መረጃ ለሌላቸው በድንብ በተግባር አስረዷቸው።
እራሳቹንም ጠብቁ ! ቸር ሁኑ ! ቸር ቸሩን ያሰማቹ !

ጆን ኦቢ ሚካኤል ከክለቡ ጋር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተለያየ. . .
ናይጄሪያዊው የቀድሞ የቼልሲ አማካኝ ጆን ኦቢ ሚካኤል በቱርክ ሊግ እየተወዳደረ ለሚገኘው ትራብዞንስፓር እየተጫወተ የነበረ ቢሆንም የቱርክ ሊግ አዲሱ ወረርሽኝ ኮሮና ቫይረስን መስፋፋት አስመልክቶ ባለመቋረጡ እና ጨዋታዎች በመቀጠላቸው ምክንያት ተከትሎ ሚካኤል ደስተኝ አለመሆኑን እና የሰዎች ሂይወት ከእግርኳስ ይቀድማል የቀረው ይቅር ጥንቅር ይበል በማለት ከክለቡ ጋር መለያየቱን አስታውቋል።