ውድ ኢትዮጵያዊን ከዛሬ ጀመሮ እጃችሁን በደንብ በመታጠብ እና ባለመጨባበት እንድታሳልፉ

መልክቱን ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድ አድርሱ
https://www.facebook.com/habeshaweeklytikusmereja/
ውድ ኢትዮጵያዊን ከዛሬ ጀመሮ እጃችሁን በደንብ በመታጠብ እና ባለመጨባበት እንድታሳልፉ

መልክቱን ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድ አድርሱ

ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደ ተናገሩት የ 48 አመቱ ጃፓናዊው ከ ቡሪክና ፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የገባው march 4 ነው

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ባለቤት ሶፊ ግሪጎሪ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።
ሶፊ ግሪጎሪ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ንግግር አድርገው ከተመለሱ በኋላ የተወሰነ የሕመም ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ለ14 ቀናት ብቻቸውን ለመቆየት መወሰናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤናቸውን ሁኔታ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከታተሉ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ቤታቸው ሆነው እንደሚሠሩ ጽ/ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል።

ኮሮና ቫይረስ በስፖርቱ ዓለም!
በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ተጫዋቾች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ትላንት ለሊት ደግሞ የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርቴታም ቫይረሱ እንደሚገኝበት ተረጋግጧል።
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የስፖርቱ ዓለም ሰዎች፦
More @TIKVAHETHSPORT

“በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው” – የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
የFDRE ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እና የሰራዊቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎችም ተሳትፈዋል።
በጉብኝታቸውም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እየተገነባ ያለውን የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

“ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ ነው!” – ዛሬ ሹመቱን ከተቃወሙ የምክር ቤት አባላት
የዛሬው የአራቱን ሚኒስትሮች ሹመት 21 የሕወሓት አባላት ተቃውመውት ነበር፡፡ ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ እንደሆነ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሕወሓት ያፈራውን ሀብት ለመቀራመት የሚደረግ ሹመት ነው የሚሉ ተቃውሞዎችም ተሰምቷል፡፡
ሌሎቹ የምክር ቤት አባላት ደግሞ በተሿሚዎቹና በሹመቱ ላይ የቀረበውን ትችት ያስተባበሉ ሲሆን ፣ ‹‹ሚኒስትሮቹ የሚሾሙት ላለፉት ዓመታት የተዘረፈ ሀብትን ለማስመለስ ነው፤›› ሲሉ ወ/ሮ ብርቱካን ታደሰ የተባሉ የምክር ቤቱ አባል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዳባ ደግሞ ዶ/ር ሊያ ከትግራይ ብሔር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ከዚህ ቀደም ሚኒስትሮችን ለመሾም የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ቡራኬ ያስፈልግ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ሹመት መስጠት በመጀመራቸው ምክንያት የቀረበ ተቃውሞ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ (ኦኤንኤን) ሁለት ጋዜጠኞቼ በመንግሥት ታሰሩብኝ ብሏል!
የታሰሩ ጋዜጠኞችም ደሱ ዱላ እና ዋቆ ኖሌ እንደሚባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶርሳ ደበላ ተናግረዋል። የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ ጋዜጠኞቹ የታሰሩት በሞያቸው ሳብያ ሳይሆን ጥፋት በመፈፀም ተጠርጥረው ነው ብሏል።
Via VOA Amharic

የINVEA 10 ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል!
በአስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶችን ያላሟሉ እና መደበኛውን ፓስፖርት ያለአግባብ ሲሰጡ የነበሩ ሰራተኞች እንደነበሩ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።
ያለአግባብ መስፈርቱን ላላሟሉ እና ለውጭ ዜጎች ፓስፖርት የሰጡ 10 ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በተደረገው የማጣራት ስራ ሰራተኞቹ ከውጭ ዜጎቹ ከ5 ሺህ ዶላር በላይ መቀበላቸውን ተገልጿል፤ 77 የሚሆኑ ፓስፖርቶች በህገ ወጥ መልኩ ተሰርተው መገኘታቸውንም ተሰምቷል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ፓስፖርቶቹ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለኢንተርፖል ማሳወቅ እና ሰዎቹን ተጠያቂ የማድረግ ስራ መስራቱ የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ገልጿል።

ፓስፖርት በ1 ወር ጊዜ ውስጥ መሰጠት ሊጀመር ነው!
የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መስጠት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል እንደገለጹት፥ ከዚህ ቀደም አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት ሁለት ወር ከ15 ቀን በላይ ይወስድ የነበረው ጊዜ ወደ አንድ ወር ዝቅ እንዲል ተወስኗል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማውጣት እስከ አምስት ቀን ብቻ እንደሚወስድም ተናግረዋል።
ካለፈው ዓመት የካቲት ወር ጀምሮ በፓስፖርት ወረቀት እጥረት ምክንያት የአዲስ ፓስፖርት መስጫ ጊዜ ከአንድ ወር ወደ ሁለት ወር ከ15 ቀን መራዘሙ ይታወሳል።
በአሁኑ ሰዓት ኤጀንሲው ከ270 ሺህ እስከ 300 ሺህ ፓስፖርት እንዳለው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በቀጣይ 500 ሺህ ፓስፖርት ለማስገባት ስምምነት መደረሱን ገልፀዋል።

ውዝግብ ያስነሳው የዲያቆን ዳንኤል ሹመት!
ዛሬ የምክር ቤት አባላት ምክር ቤቱ ሹመት በመስጠትና በመንፈግ ላይ መጠመዱን በማንሳት ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል።
ለኢትዮጵያ የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ ያቀረቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳሉት ከሆነ ግለሰቡ የሀይማኖት እኩልነት ላይ የማያምኑ፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩ፣ በማለት በሕዝብ የሚነሱባቸው ቅሬታ ወደ ጎን በመተው መቅረብ አልነበረባቸውም በሚል አባልነታቸውን ተቃውመዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መላውን ኢትዮጵያ የሚያገለግል በመሆኑ በእርሳቸው የቦርድ አባልነት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡት አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ በመቅረቡ ለብቻው ጉዳያቸው ታይቶ ድምጽ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ በ148 ድጋፍ በ126 ተቃውሞ እና 24 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የዲያቆን ዳንኤል የቦርድ አባልነት ፀድቋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ