የኮሮና ቫይረስ “አለም አቀፍ ወረርሽኝ” ተብሎ ታውጇል!
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ዛሬ ቫይረሱ ያለበትን ሁኔታ ካሳወቁ በሁዋላ “አሁን አለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለዋል።
ቫይረሱ እስካሁን ከ3,000 በላይ ሰዎችን ገድሎ ከ120,000 በላዩን ደግሞ አጥቅቶ ይገኛል።
@eliasmeseret
https://www.facebook.com/habeshaweeklytikusmereja/

የኮሮና ቫይረስ “አለም አቀፍ ወረርሽኝ” ተብሎ ታውጇል!
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ዛሬ ቫይረሱ ያለበትን ሁኔታ ካሳወቁ በሁዋላ “አሁን አለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለዋል።
ቫይረሱ እስካሁን ከ3,000 በላይ ሰዎችን ገድሎ ከ120,000 በላዩን ደግሞ አጥቅቶ ይገኛል።
@eliasmeseret

ዶክተር ሊያ ታደሰ በነገው ዕለት የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ሆነው እንደሚሾሙ መስሪያ ቤታቸው አረጋገጠ። ዶክተር ሊያ የጤና ምኒስትር ድኤታ ሆነው የተሾሙት ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር።

በተመሳሳይ በወይዘሮ አዳነች አቤቤ ምትክ የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው አቶ ላቀው አያሌው ሊሾሙ እንደሚችሉ አዲስ ፎርቹን ይፋ አድርጓል። አቶ ላቀ አያሌው የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው አገልግለዋል።
Addis fortune

የ20/80 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለዕድለኞች ሊተላለፉ ነው!
የተገነቡት “በኦሮሚያ ክልል ላይ ነው” በሚል ውዝግብ ተቀስቅሶባቸው ከነበሩ የአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ ሰላሳ ሁለት ሺህው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ሊተላለፉ እንደሆነ ሪፖርተር ዘግቧል።
እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ የኮንዲሚኒየም ቤቶቹን ውዝግብ እንዲያጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ተውጣጥቶ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ ዕጣ ከወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 9,000 ያህሉ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መገንባታቸውን አረጋግጧል።
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ!
በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ሰሞኑን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተያዘው ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡
ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ተነጋግሮና መፍትሔ አስቀምጦ ስምምነት ላይ ሳይደረስ፣ ቤቶቹን ለዕድለኞቹ ለማስተላለፍ ውል መፈጸም በቀጣዩ ሒደት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡
More https://telegra.ph/Reporter-03-11
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

ወፍሪ ሓርነት!
በመንግስት በኩል እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው 14 የትግራይ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እስካሁን የተለቀቁት 11 ብቻ መሆናቸውን ወፍሪ ሀርነት አስታወቀ።
ወፍሪ ሀርነት በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ የትግራይ አስረኞችን መብት ለማስከበር የተቋቋመ ኮሚቴ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥቷል።
የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች፦
• መንግስት የካቲት 16 ቀን 2012 ምሽት ላይ እንዲፈቱ ውሳኔ የተላለፈላቸው 14 ሲሆኑ የተለቀቁት 11 ብቻ ናቸው።
• የተፈቱትም ቢሆን በተንጠባጠበ መልኩ የተለቀቁ ናቸው። ይህ ሂደት ግልፅኝነት የጎደለው እና የታሳሪ ቤተሰቦችን ያሳቀቀ ተግባር ነው።
• መንግስት በወቅቱ ያወጣቸው በነበሩ መረጃዎች 60 ትግራዋይ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ የሚያመላክት የነበረ ቢሆንም እንዲፈቱ ትዕዛዝ የተላለፈላቸው ግን 14 ብቻ ናቸው።
• መንግስት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ካሳለፈላቸው 61 እስረኞች ውስጥም 3 ያልታሰሩ የነበሩ እንዲሁም ሁለቱ ከዚህ በፊት ታስረው ከተፈቱ አንድ ዓመት ያለፋቸው፣ ሰባቱ ደግሞ ጥቅምት ታስረው አሁን የተፈቱ ናቸው።
• ለውጥ ላይ ነን እየተባለ አሁንም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትግራይ የፖለቲካ እስረኞች በፌደራል፣ በክልሎች እና በሌሎች ድብቅ እስር ቤቶች ላለፉት ሁለት ዓመታት ታስረዋል፤ መንግስት እነዚህን እስረኞች ሊፈታ ይገባል።
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
ተጨማሪ መረጃ፦
ቢቢሲ የካቲት 25 እና 26/2012 ዓ.ም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ጉራጌ ዞን ኮኪር ገደባኖ ጉታዘር ወረዳ፤ መሃል አምባ ከተማ የሚገኝ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ላይ ጥቃት መድረሱን የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ይልማ ሙሉጌታ መናገራቸውን ዘግቧል።
መጋቢ ይልማ ቤተክርስቲያኒቷ በአካባቢው ከ25 ዓመት በላይ የኖረች መሆኗን ጠቅሰው “በአካባቢው የሚገኙ የሐይማኖት አክራሪዎች ከምሽቱ 3፡30 ላይ አፍርሰዋታል” ሲሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም በወቅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ምዕመናን ላይም ድብደባ መፈፀሙንና ሰባት ምዕመናን መታሰራቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገርም ቀደም የነበረው የአምልኮ ቦታ ሙሉ በሙሉ መቃጠሉንና የነበረው ንብረት መውደሙን ተናግረዋል።
ታስረው ከነበሩት ሰባት ምዕመናን መካከል ስድስቱ ትናንት መፈታታቸውን የሚናገሩት መጋቢ ይልማ፣ አንዱ ግን አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በከተማው የሚገኙ ከ40 በላይ የቤተክርስቲያኒቷ አባላት ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ጎረቤት ወደ ሆነው የኦሮሚያ ክልል በመሸሽ በሀርቡ ጩልሌ ሙሉ ወንጌል ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
ምንጭ፦ BBC
በሞረትና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሄደ ቡድን ላይ ጥቃት ደረሰ!
በአማራ ክልል ሞረትና ጅሩ ወረዳ፣ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጡ የመጡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሐይማኖት ስብከት ለምን ያካሂዳሉ በሚል ጥቃት እንደደረሰባቸው የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ተናገሩ።
ወደ ከተማዋ ያቀናው የሕክምና ቡድን 18 የውጪ አገር ዜጎች የተካተቱበት ከ200 በላይ አባላት ያሉት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ወጋየሁ ቦጋለ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ይልማ ሙሉጌታ በበኩላቸው በእነዋሪ ከተማ ለ20 ዓመት የነበረ ቤተ እምነት ላይ ጥቃትና ዘረፋ መፈፀሙን አረጋግጠዋል።
መጋቢ ይልማ አክለውም ጥቃቱ የተፈፀመው በሐይማኖት አክራሪዎች ነው ያሉ ሲሆን ንብረቶች መዘረፋቸውን፣ ሦስት ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል እንደሚገኙ እና ቃጠሎ መፈፀሙን ተናግረዋል።
More https://telegra.ph/BBC-03-11-2
ምንጭ፦ BBC