
ProsperityParty
ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ግዙፍ የተባለ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚያካሂድ ዋዜማ ራዲዮ ዘገበ። በቅዳሜው መርሀ ግብር ላይ እንዲሳተፉም በርካቶች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ነው የተባለው። ባለሀብቶች፣ ምሁራንና የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙም ተነግሯል።
የቅዳሜው የሚሊኒየም አዳራሽ መርሀ ግብር “የብልጽግና ፓርቲ የማጠናከሪያ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የመጀመርያው ምእራፍ ማብሰሪያ የእራት ግብዣ” የሚል ስያሜ አለው ነው የተባለው። በቅዳሜው የእራት ግብዣ ላይ ለብልጽግና ፓርቲ በይፋ ገንዘብ የማሰባሰብ መርሀ ግብር የማከናወን እቅድ ይኑር አይኑ መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ ሬድዮ ጣቢው ጨምሮ ገልጿል።
ለምርጫ ዘመቻ የፖለቲካ ስራ ገንዘብን በተለያየ መልኩ በድጋፍ ማሰባሰብ በሌሎች ባደጉ ሀገራት የተለመደ ቢሆንም አሁን በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተደረጉ ያሉ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎች ግን በተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጫና በመፍጠር የተከናወኑ ናቸው በሚል ከዚህ ከዚያም ወቀሳዎች ይደመጣሉ።
ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ








